ሆራይዘን አዲስ ጎማ ኃ/የተ/የግ/ማ 10ኛውን ሐገር አቀፍ የጥራት ሽልማት በአንደኛ ደረጃ፤ ሰሚት ኢንጂነርድ ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማ ሁለተኛ ደረጃ በመሆን ሁለቱም የሚድሮክ ድርጅቶች አሸነፉ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት እና የኢትዮጵያ ጥራት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ በታላቁ ቤተ-መንግስት ሀገር ዓቀፍ የጥራት ሽልማትን ሰጥተዋል።

በአጠቃላይ ዘጠኝ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኩባንያዎች በመርሀ- ግብሩ ተሸላሚ በመሆን የመድረኩ ድምቀት ሆነው አምሽተዋል። እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ።

ዛሬ ሕዳር 15/2016 ዓ.ም ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት እና የኢትዮጵያ ጥራት ድርጅት የበላይ ጠባቂ በተገኙበት በታላቁ ቤተ-መንግስት ሐገር ዓቀፍ የጥራት ሽልማት አሰጣጥ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

በዚህ መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ስር የሚገኘው ሆራይዘን አዲስ ጎማ ኃ/የተ/የግ/ማ በአንደኝነት የልዩ የወርቅ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ሰሚት ኢንጂነርድ ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማ በብር ደረጃ በሁለተኝነት ተሸላሚ የሆነ ሲሆን ሌሎች ሰባት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድርጅቶችም የተሸለሙ ሲሆን በጠቅላላው 9 ድርጅቶቻችን የጥራት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በዛሬው ምሽት የተሸለሙት ድርጅቶቻችን ዝርዝር

* ሆራይዘን አዲስ ጎማ ኃ/የተ/የግ/ማ

* ሰሚት ኢንጂነርድ ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማ

* አንሊሚትድ ፓኬጂንግ ኃ.የተ.የግ.ማ

* ፋርማኪዩር ኃ.የተ.የግ.ማ

* ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ.

* አዲስ ጋዝ እና ፕላስቲክ ኃ.የተ.የግ.ማ.

* ዘመናዊ የህንፃ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. (ኤም.ቢ.አይ)

* ኮንቦልቻ የብረታብረት ማምረቻ ኢንደስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. (ኮስፒ)

* ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማ ናቸው።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በዚሁ ጊዜ ተቋማት ጥራትን የሥራቸው ማዕከል አድርገው ሊሠሩ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተቋማት ከተቀመጠ ስታንዳርድ ጋር ውድድር በማድረግ የምርትና የአገልግሎታቸውን ጥራት ለማስጠበቅ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ዛሬ ለሽልማት የበቁ ተቋማት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ድርጅቱ በየዓመቱ የሚያከናውነው ሽልማት የተቋማትን አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ተቋማት በውድድር ሂደቱ ተሞክሮዎች፣ የሚሰጣቸውን ጠቃሚ አስተያየቶች የእቅዶቻቸው አካል በማድረግና ተቋማዊ አሠራሮችን በማስፈን ዘመን ተሻጋሪ መለያ ለመፍጠር መትጋት አለባችሁ ብለዋል።

በተጓዳኝም ያሏችሁን ጥንካሬዎች በማስቀጠል እንዲሁም መስተካከል የሚገባውን በማረም በቀጣይም ተቋማት ምርትና አገልግሎት ጥራት በማረጋገጥ ለሀገሪቱ እድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም “ተቋማት ጥራትን የሥራቸው ማዕከል ሊያደርጉ ይገባል” ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት አምራቾችን፣ አገልግሎት ሰጪዎችና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ድርጅቶችን በማወዳደር እውቅናና ሽልማት የሚሰጥ ድርጅት ነው።

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY