ለአርሶአደሩ የቴክኖሎጂ ሽግግር- ሚድሮክ ለሀገር : ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 60 ቡና መቀሸሪያ ማሽኖችን ለኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሮች አበረከተ።
ማሽኖቹ በሰዓት የታጠበ ቡና ከነሸሚዙ 400 ኪሎ ግራም እና ጀንፈል ቡናን 120 ኪሎ ግራም መቀሽር የሚችሉ ናቸው።
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ሚድሮክ በክልሉ እየሰራ ላለዉ የኢንቨስትመንትና ማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
ሚድሮክ ትርፋማነትን ከማስቀደም ይልቅ ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ብለዋል።
ሚድሮክ ሁሌም ከሀገር ልማት ጎን በመሆኑ ዜጎች ተቋሙን መጠበቅ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
የጂማ ዞን አስተዳዳሪ ቲጃኒ ናስር ሚድሮክ ከማትረፍ ይልቅ ህዝብን በማገልገል ላይ የሚገኝ ተቋም በመሆኑ እንደ ዓይናችን ብሌን እንጠብቀዋለን ብለዋል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ሚድሮክ የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ በተለይም ቡናን ሜካናይዝድ በማድረግ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በስፋት በመስራት አርሶ አደሩ ጥራት ያለው ቡና ለገበያ እንዲያቀርብና ከምርቱ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ጀማል አህመድ።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከትርፉ 10 በመቶውን ለማህበራዊ ሃላፊነት በማዋል የሚታወቅ እና በኢትዮጵያ ከ79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ የሀገር ሀብት ነው።
ሚድሮክ – ለሀገር! ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ












