ይህን ለማሳካት ደግሞ የመንግስትና የግሉ ዘርፎች አስተዋፅኦ በእጅጉ ያስፈልጋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕም በኢትዮጵያ ከግሉ ዘርፍ በተለየ ሁኔታ በግብርና ዘርፍ የተፈጥሮ ጸጋዎችን ከዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋር በማስተሳሰር ለሀገር እድገት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኘው ኢትዮ አግሪ ሴፍት መቀመጫውን ዛምቢያ ካደረገው ዛም ሲድ ከተባለ ዓለም አቀፍ ኩባንያ በአንደኛ ደረጃ ሽልማት አግኝቷል።
ሽልማቱንም ያገኘው ላለፉት ሶስት ዓመታት የዛም ሲድ አዲስ የበቆሎ ዝርያን ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች በማስተዋወቅ፣ ከምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ከተቋሙ ጋር ከሚሰሩ ድርጅቶች የተሻለ አፈጻጸም በማሳየቱ ነው።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ZMS721 (ወርቅማ) የተሰኘ የበቆሎ ዝርያ ለጎጃም አካባቢዎች፣ ሐዋሳ፣ ነገሌ አርሲ፣ ጉራጌ ዞን፣ ጂማና ሌሎች አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች በማስተዋወቅ መጠቀም የጀመሩ ሲሆን፣ ቀድሞ ይጠቀሙት ከነበረው አንጻር ከፍተኛ ለውጥ አምጥተውበታል።
የበቆሎ ዝርያው በምርታማነቱና በሽታን በመቋቋሙ የሚታወቅ ሲሆን፣ በሄክታር ከ80 ኩንታል በላይ ምርት መስጠት የሚችል ነው። የሀገሪቱን የበቆሎ ምርታማነት በእጅጉ ለማሳደግ ዝርያውን የበለጠ ለገበሬዎች የማስተዋወቅ ስራ በቀጣይነት የሚሰራ ይሆናል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሀገርን ለማሳደግ ከሚሰራባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ግብርና አንዱ ሲሆን፤ ዘርፉን በማዘመን፣ ምርታማነትን በማሳደግ፣ ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለመጨመር፣ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስፋት በመስራት ላይ ይገኛል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት









