ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና ሌሴቶ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አደረጉ።

በኢትዮጵያ የሌሴቶ አምባሳደር እንትጺዋ ካስቲሊያ ሴኬቴ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮች ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ዉይይት አድርገዋል።

አምባሳደሯ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ በተለይም ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሀገር ውስጥ ያለውን አቅም ወደ ሌሴቶ በማምጣት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሰማራም አምባሳደሯ ጥሪ አቅርበዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ አበበ ተክሉም ግሩፑ ከሌሴቶ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በደቡባዊ አፍሪካ የምትገኘው ሌሴቶ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች እንዳሏት አምባሳደሯ ገልጸዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በንግድና አገልግሎት፣ በሆስፒታልቲ እንዲሁም በኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፎች የተደራጁ 45 ኩባንያዎችን ያቀፈና 79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፈጠር የቻለ ተቋም ነው ።

ሚድሮክ ለሀገር- ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY