ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና ካርፉር የቢዝነስ ቅንጅት (የፍራንቻይዝ) ስምምነት አደረጉ።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ የተደረገው ስምምነት ሚድሮክ ሀገርን ለማሳደግ በቁርጠኝነት በመስራቱ የተገኘ ዉጤት ነው ብለዋል። ይህም የኢትዮጵያ ንግድን ለማዘመን ትልቅ እርምጃ ነው ያሉት።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ስምምነቱ ለኩዊንስ ሱፐርማርኬት የዕድገት ጉዞና ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘዉን ዉጤት ለማሳድግ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ገልጸዋል።

17 ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በጂማ፣ በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በድሬደዋ፣ በደሴ፣ በባህርዳርና በጎንደር ከተሞች እንደሚከፈቱም ገልፀዋል።
በተለይም ሚድሮክ የቡና፣ የሻይ ቅጠል፣ የቅመማቅምና የአበባ ምርቶችን ለካርፉር በማቅረብ የዉጪ ምንዛሬን ለማስገኘት እንደሚሰራ ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
የካርፉር ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ላስፈርጉስ ስምምነቱ የሀገር ውስጥ ሸማቾችን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርቶችን ለዓለም ገበያ እንዲቀርቡ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል ።
በሁለቱ ተቋማት የተደረገው ስምምነት በዘርፉ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ፍራንቻይዝ (franchise) ለኢትዮጵያ ገበያ ያስተዋወቀ ነው።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው ኩዊንስ ሱፐርማርኬት በአዲስ አበባ 13 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ምርቶችን በተመጣጠኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን በማረጋጋት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ የሚገኝ ነዉ።

የፈረንሳዩ ካርፉር ሱፐር ማርኬቶችን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ከ15 ሺህ በላይ መደብሮች ያሉትና በዘርፉ በዓለም ላይ የሚታወቅ ድርጅት ነዉ፡፡

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ -የሀገር ሀብት

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY