ድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – ሚድሮክ ለሀገር
ህፃን ብሌን አሸናፊ ባለፉት 10 ዓመታት በከፍተኛ የአንጎል ውስጥ ውሃ እና የአንጎል ግፊት መጨመር (ሀይድሮሴፋለስ) ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆናለች።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመኖሪያ ቤቷ ተገኝተው ለህክምናዋ የሚያስፈልጋትን 4 ሚሊዮን ብር ለወላጅ አባቷ አስረክበዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቤተሰቡ በአሁኑ ወቅት የሚኖርበት ቤት ለህፃኗ የፊዚዮቴራፒ ህክምናም ሆነ ለጤንነቷ አመቺ ባለመሆኑ፣ አስተዳደሩ ለቤተሰቡ የተሻለ መኖሪያ ቤት እንዲያገኝ ውሳኔ ማስተላለፉን ገለፀዋል።
ህፃን ብሌን ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ አስፈላጊውን ህክምና እንድታገኝ በሀኪሞች ቢታዘዝላትም፣ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እስካሁን ሳይሳካላት ቆይቷል።
ከንቲባዋ ባደረግንላቸው ጥሪ መሰረት ይህንን በጎ ተግባር በመደገፍ፣ የብሌንን አጠቃላይ የህክምና ወጪ ለሸፈኑት ለክቡር ሼይኽ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል-አሙዲ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ በለዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሰዉ ተኮር ድጋፎች ላይ በቀዳሚነት በመሳተፍ ለሀገርና ለወገን ደራሽ መሆኑን የሚያሳዩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው።
የብሌን አባት ወጣት አሸናፊ በጽዳት ሰራተኝነት ተቀጥሮ እየሰራ ያለ እናት እርዳታ ብሌንን፣ ታናሽ እህቷን፣ ሌላኛዋን አካል ጉዳተኛ እህቱን እና በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ አገልግለው ጡረታ የወጡ አቅመ ደካማ እናቱን የሚንከባከብ፣ ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ጠንካራ ወጣት ነው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ-ሚድሮ








