ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለአዲስ አበባ ከተማ ሰው ተኮር ስራዎች ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ልዩ ተሸላሚ ሆነ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ላከናወናቸው ሰው ተኮር ስራዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ልዩ እውቅና ተሰጥቶታል።

በተለይም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀ-መንበር ሸይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲን ራዕይ ለማሳካት ቁርጠኛ አመራር በመስጠት በደሀ ተኮር ስራዎች ላይ ግንባር ቀደም ሚና እየተወጡ ያሉት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ሽልማቱን ተቀብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው በፍቅር ላካፈሉ ልበ ቀና ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እውቅና እና ሽልማት ሰጥተው አመስግነዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እውቅናውን በተመለከተ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፈዋል።

…”አዲስ አበባችን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት መዲና እንድትሆን ያደረግነው ጥረትና ልፋት ፍሬ አፍርቶ በእናንተ ቅንነት እና በጎነት የበርካቶችን እምባ አብሰን የመኖር ተስፋቸውንም አለምልመናል::

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ35 ሺሕ በላይ ቤቶችን እንዲሁም ባለፈው አንድ ዓመት ደግሞ 7,567 ቤቶችን ገንብተን ለአቅመ ደካሞች በማስተላለፍ ኑሯቸውን አቃንተናል::

በ2016 በጀት ዓመት ብቻ 12 ቢሊዮን ብር በበጎ ፈቃድ የማስተባበር እንዲሁም በዚህ ዓመት ብቻ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ማዕድ በማጋራት ለወገኖቻችን አለኝታነታችንን አሳይተናል።

መስጠት አያጎድልም በማለት በቅንነት ለወገን የተረፈ የበጎ ፈቃድ ስራ ላይ የተሳተፋችሁ ልበ ቀና ባለሀብቶች እንዲሁም ያስተባበራችሁና የመራችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች እምባቸው በታበሰ እና ኑሯቸው በተቃና ዜጎቻችን እንዲሁም በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::”

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት በርካታ ደሀ ተኮር ስራዎችን ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ጋር በመተባበር አከናውኗል።

የመኖሪያ ህንፃዎች ግንባታ፣ የምገባ ማዕካላት ግንባታና ቀጣይነት ያለው የምገባ አገልግሎት፣ ዘመናዊ የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካ ግንባታ ላይ ተሳትፎ፣ ፅዱ ኢትዮጵያ፣ የኩላሊት ዲያሊስስ ማሽንና ግብዓት ልገሳ፣ የከተማ ግብርና፣ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እንዲሁም የማዕድ ማጋራት ፕሮግራምን በአብነት ማንሳት ይቻላል።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY