ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለኩላሊት ህሙማን ታካሚዎች የሚያገለግሉ 10 ዘመናዊ የሕክምና አልጋዎችን ለምኒሊክ ሆስፒታል በስጦታ አበረከተ።
አልጋዎችን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማህበራዊ ሃላፊነት ዳይሬክተሩ አምባሳደር አሊ ሱሌማን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ አስረክበዋል።
የቢሮ ሃላፊው በርክክቡ ወቅት እንዳሉት ሚድሮክ ከዚህ ቀደም ለኩላሊት ህሙማን ታካሚዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከሌሎች የቢዝነስ ተቋማት በተለየ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የሚደርገው ጥረትም የሚደነቅ ነው ብለዋል ዶክተር ዮሃንስ ጫላ።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዚህ በፊት በ170 ሚሊዮን ብር ወጭ ለኩላሊት እጥበት የሚያገለግሉ ማሽኖችና የሶስት አመት የህክምና ግብዓት ድጋፍ ማድርጉ ይታወሳል ።
ሚድሮክ ከሚያገኘው ገቢ 10 በመቶውን ለማሕበራዊ ኃላፊነት በመመደብ ሀገራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ያለ የህዝብ ሀብት ነው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2017 አ.ም በጀት አመት ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት 2.2 ቢሊዬን ድጋፍ በማድረግ ላበረከተው አስተዋጽኦ በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ሽልማት ተበርክቶለታል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ-የሀገር










