ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሻይ ቅጠል ምርትና ኤክስፖርት፣ በቡና ላኪነትና በሜካናይዝድ የቡና እርሻ ልማት ዘርፍ ተሸላሚ ሆኗል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  በአጠቃላይ 3 ሽልማቶችን አግኝቷል።

ሽልማቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ  ከኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እጅ  ተቀብለዋል።

በሳይንስ ሙዚየም “ፈጠራና እና ፍጥነት ለቡናችን ስኬት” በሚል መሪ-ቃል በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የቡና ኤግዚቢሽንና እዉቅና መርሐ ግብር ላይ ነው ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሽልማቱ የተሰጠው።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጥራታቸውና በጣእማቸው ልዩ የሆኑ የተለያዩ የቡና ምርቶችን በማምረት ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ ያለ ተቋም ነው።

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የቡናና የሻይ ቅጠል እርሻዎቹ ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጨማሪ የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአመታዊ ትርፉ አስር በመቶውን ለማህበራዊ ሃላፊነት በመመደብ ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ የሀገር ሀብት ነው።

ሚድሮክ ለሀገር – ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY