ሆቴሎቹ ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ተኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሸራተን አዲስ ኤ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ እጅግ ዘመናዊ የሆነና የሸራተን አዲስ ሆቴልን ስያሜ የሚይዝ ሌላ ሆቴል ይገነባል።
በሚሊኒየም አዳራሽ ቅጥር ግቢ ዘመናዊ ሆቴል (Moxy by Marriott) ፣ በመሀመድያ የመኖሪያ መንደር (Four Points by Sheraton) ሆቴሎች ይገነባሉ።
በቅርቡ የሚድሮክን ቤተሰብ የተላቀለው ዋቢሸበሌ ሆቴል (autograph collection by Marriot) ደረጃ ለጉባኤው ዝግጁ ይሆናል።
አፍሪካ ህብረት አጠገብ እየተገነባ ያለው ዌስት ኢን አዲስ (Westin Addis) ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለ32ተኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተሳታፊዎች 1500 አልጋ ያላቸው ሆቴሎችን እንደሚገነባ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል።
በተጨማሪም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በክልል ከተሞች በጂማ እና ሃዋሳ (Four Points by Sheraton) ሆቴሎችን እየገነባ ይገኛል።
በባህርዳር ከተማ ደግሞ (Four Points by Sheraton) እና (Protea by Marriott) ለመገንባት ዝግጅቱን አጠናቋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቅርቡ የላንጋኖ ሳቫና ሪዞርትን በግዥ የተረከበው ሲሆን በማርዮት ብራንዶች አለም አቀፍ ሪዞርት በመገንባት ወደ ስራ ይገባል።
ባሳለፍነው ሳምንት የኤኮ ቱሪዝም ዘርፉን ከፍ ሊያደርግ የሚችለውን የደንቢ ኤኮ ሎጅ በማስመረቅ ወደ ስራ አስገብቷል ።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት











