ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው።

አውሮፕላን ማረፊያ መሰረት ድንጋይ – ሚድሮክ ለሀገር

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው።

የግንባታ መሰረተ ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አስቀምጠዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት፣ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባሰለፈነዉ 2017 ዓ.ም በሻኪሶ ከተማ ያስገነባዉ የሚድሮክ ወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ/የተ/የግ/ማ ለሻኪሶ ከተማና ለአከባቢው ማህበረሰብ መንገድ በመሰራት፣ የመጠጥ ዉሃ በማስገባት፣ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት እና ሌሎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

አሁንም ሚድሮክ የከተማዋን እድገት ለማፋጠንና የአከባቢውን ማህበረሰብ የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጡ ደስታ ይሰማዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው መስከረም 2019 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY