ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በዓለም የከተሞች ፎረም (World Urban Forum) ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

‎ፎረሙ በተባበሩት መንግሥታት (UN-Habitat) አስተባባሪነት በባኩ፣ አዘርባጃን የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በፎረሙ ላይ እየተሳተፉ ነው።
‌‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለኢትዮጵያ ከተሞች እድገት በተለይም በኮንስትራክሽንና ሪል-ስቴት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ሚና እየተጫወተ የሚገኘው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በፎረሙ ላይ መሳተፉ የተሻለ የልምድ ልውውጥ እንዲያገኝ ያስችለዋል።
‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በመንገድ፣ በሕንጻ፣ በስታዲየም ግንባታ፣ በኮንክሪት ምርትና በአስፓልት ፕላንት እንዲሁም በአሸዋ ምርት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ፣ በኢትዮጵያ የዘመናዊ ግንባታ ሂደት ውስጥ የቀዳሚነት ሚናን በመጫወት ላይ የሚገኝ ኩባንያ ባለቤት ነው።
‎ግሩፑ በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነባ ያለውን ግዙፉን የመሀመዲያ ፕሮጀክትን ጨምሮ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሕንጻዎችን፣ መንገድ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ስታዲየሞችን በመገንባት ላይ ይገኛል።

‎የዓለም የከተሞች ፎረም የከተሞችን ቀጣይነት ያለው ዕድገት በሚያፋጥኑ ስትራቴጂዎች፣ የከተሞች መኖሪያ ቤት ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችሉ ሁኔታዎች፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ የከተሞችን የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘመን በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች እና በተለያዩ የከተማ ልማት ፖሊሲዎች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረግን አላማ አድርጎ የሚካሄድ ጉባኤ ነው ነው።

‎በዚህ ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ሚድሮክን ጨምሮ ከተለያዩ የዓለም አገራት የተወጣጡ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች፣ የከተሞች አስተዳዳሪዎች፣ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት (UN) ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY