ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2017/2018 በጀት ዓመት ከአጠቃላይ ሽያጭ የዕቅዱን 99% ማሳካቱን አስታወቀ፡፡

‎‎አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ52 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

‌‎ለግብር እና ሌሎች መንግስታዊ ግዴታዎች ከ31 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገ ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ62 በመቶ በላይ ከፍ ያለ መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።

‎ተቋሙ ከትርፍ አንጻር የእቅዱን 105 በመቶ በማሳካት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ69 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ሪፖርቱ አመላክቷል።

‎በበጀት አመቱ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሰራተኛ ደሞዝ ክፍያ ከ8.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማደረጉ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

‎ግሩፑ በበጀት ዓመቱ ለውጪ ገበያ ካቀረባቸው ምርትና አገልግሎቶች ከ390 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለሀገር ያስገኘ ሲሆን‎ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ50 በመቶ ጭማሪ ያለው መሆኑ ተጠቅሷል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በበጀት ዓመቱ ከ1∙3 ቢሊዮን ብር በላይ በገንዘብና ሌሎችም በአይነት የተሰጡ የተለያዩ የማህበራዊ ድጋፍ ስራዎች አከናውኗል፡፡

በእያንዳንዱ ድርጅት ደረጃም በተናጠል ከ355 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ በገንዘብ፣በአይነትና በፕሮጀክቶች ልማት ወጪ ተደርጓል፡፡

‎የበጀት አመቱ እቅድ አፈጻጸም በተገመገበት መድረክ ላይ የተገኙት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ በሁሉም ዘርፎች የተገኙ ዉጤቶች አበረታች መሆናቸውን ገልፀዉ ሚድሮክ ዘመኑን የዋጀ አሰራሮችን ተከትሎ መስራት አለበት ብለዋል።

‎የፕሮጀክት አፈፃፀምና የአሰራር ስርዓቶችን በማዘመን የበለጠ የተቋሙን ዉጤታማነትና ቀጣይነት በሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው።

‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሀገር ዉስጥና በዓለም ገበያ ያለዉን ድርሻ በማሳደግ፣ምርትና ምርታማነትን በመጨመር፣የማርኬቲንግ ስራዎችን በማቀላጠፍና አሰራሮችን ዲጅታላይዝ በማድረግ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

‎ሁላችንም የሚድሮክ ሠራተኞች የተቋሙን እሴቶች ማለትም ለምንሰራቸው እያንዳንዱ ስራ በተሰጠን የሃላፊነት ልክና ደረጃ ተጠያቂነትን እያሰፍንን፣ ኃላፊነታችችንን በልኩ እየተወጣን ፣ ለምንሰራው እያንዳንዱ ስራ ግልጽኝነትን መርህ አድርገን ፣ከሁሉም በላይ ደግሞ ሚድሮክ የእኛ፣ የልጆቻችን፣ የቤተሰብ እና የሀገር ሀብት መሆኑን በመገንዘብና በባለቤትነት ስሜት ከራሳችን ጋራ በማዋሃድ በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።

በሚቀጥለው አመት የተጀመሩትን ግዙፍ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ብክነትን በተቆጣጠረ ዘዴ ለመፈፀም ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አሰራሮችን ማዘመንና ተጨማሪ የስራ እድሎችን በመፍጠር ሀገራዊ ሀላፊነቱንም በታላቅ ቁርጠኝነት ይወጣል ብለዋል።

‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በስድስት ዘርፎች የተደራጁ ከ45 በላይ የሚሆኑ ድርጅቶችን በስሩ ያቀፈና በአሁኑ ወቅት 80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ተቋም ሲሆን ከትርፉ 10 በመቶውን ለማህበራዊ ሃላፊነት በመመደብ ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ የሀገር ሀብት ነው።

‎ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY