አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ71 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የ2017/2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን በሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ገምግሟል።
ተቋሙ ከትርፍ አንጻር የእቅዱን 176 በመቶ በማሳካት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ95 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ሪፖርቱ አመላክቷል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በግማሽ አመቱ ለግብርና ሌሎች መንግስታዊ ግዴታዎች ከ 18.4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡
ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ166 በመቶ በላይ ከፍ ያለ መሆኑን በሪፖርት ላይ ተገልጿል።
በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሰራተኛ ደሞዝ ክፍያ ከ4.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማደረጉን በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ግሩፑ በግማሽ ዓመቱ ለውጪ ገበያ ካቀረባቸው ምርትና አገልግሎቶች ከ155 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለሀገር አስገኝቷል።
ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ53 በመቶ ጭማሪ አለው፡፡
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ በሁሉም ዘርፎች የተገኙ ዉጤቶች አበረታች መሆናቸውን ገልፀዉ በማርኬቲንግ፣ በምርትና ወጪ ቅነሳ ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
የፕሮጀክት አፈፃፀምና የአሰራር ስርዓቶችን በማዘመን የበለጠ የተቋሙን ዉጤታማነት ቀጣይነት በሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው።
ሚድሮክ በሁሉም ዘርፎቹ ለሀገር ኩራት የሚሆኑ ፕሮጀክቶቹን በከፍተኛ ጥራት በማጠናቀቅ በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ወደ ስራ ማስገባቱን አቶ ጀማል ተናግረዋል።
በተያዘው በጀት አመት እጅግ ግዙፍ የሆኑ አዳዲስ ፕሮጀክቶች የተጀመሩ በመሆኑ በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ሁሉም የግሩፑ አመራር በባለቤትነት ስሜት እንዲቀሳቀስ አሳስበዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሀገር ዉስጥና በዓለም ገበያ ያለዉን ድርሻ በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
በተያዘው በጀት አመት ባለፉት ስድስት ወራት የሀገር ኩራት የሆኑት ደንቢ ኢኮሎጅና አርጆ የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ተመርቀው ወደ ስራ መግባታቸው ይታወሳል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በስድስት ዘርፎች የተደራጁ ከ45 በላይ የሚሆኑ ድርጅቶችን በስሩ ያቀፈና በአሁኑ ወቅት 80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ተቋም ነው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – ሚድሮክ የሀገር ሀብት










