ፋብሪካውን ገንብቶ ለማጠናቀቅ 6 ወራት ጊዜ ብቻ የወሰደ ሲሆን፤ ይህም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ፋብሪካዎችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ማስረከብ መገለጫው እየሆነ ለመምጣቱ አንዱ ማሳየ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ
ፋብሪካውን በመመረቅ ስራ ያስጀመሩት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሲሆኑ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ የማዕድን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዱላ መኮንን የየዘርፎቹ ምክትል ስራ አስፈፃሚዎችና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ፋብሪካው የኤስ.ፒ.ሲ የወለል ንጣፎችን በእንጨት፣ በድንጋይና በእምነበረድ ተፈጥሯዊ ዕይታን ጠብቀው በ25 ዓይነት ቀለማት እና ዲዛይን ቀርበዋል፡፡ የቀለማቱን ቁጥር በቅርቡ 50 ለማድረስ እንደታቀደም ተነግሯል፡፡

ምርቱ እሳትን የሚቋቋም፣ የማያዳልጥ፣ በቀላሉ የሚገጣጠም፣ ለማጓጓዝ አመችና ቀላል፣ ከባድ ጭነትን የሚቋቋም፣ ድምጽና ቅዝቃዜን የሚከላከል ሲሆን ዋጋው ከሴራሚክ የወለል ንጣፍ እጅግ ቅናሽ ነዉ ተብሏል፡፡
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ፋብሪከዉ 70% የሚሆነውን የምርት ግብአቶችን ከሀገር ውስጥ ስለሚጠቀም የውጭ ምንዛሪን በማስቀረት የሀገሪቱን ኢኮኖሚን ለመደገፍ ትልቅ ሚና እንዳለዉ ገልጸዋል።
የክብር እንግዳው አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባደረጉት ንግግር ሚድሮክ በሀገር አቀፍ ደረጃና በክልሉ ለሚሰራቸዉ የልማት ስራዎች፤ የማህበራዊ ሀላፊነትና ግብርን በታማኝነት በመክፈሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡



በኦሮምያ ክልል ሰፊ የኢንቨስትመንት እምቅ ሃብት ስላለ ሌሎች ባለሃብቶችም የሚድሮክን ፈለግ በመከተል ወደ ስራ እንዲሰማሩ ጋብዘው ለወደፊቱም ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ይህን የመሰለ ግዙፍ ፋብሪካ በስድስት ወራት ብቻ የግንባታ ስራዉን በማጠናቀቁ ምሳሌነት ያለውን ስራ ሰርቷል ብለዋል።
የመዓድን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዱላ መኮንን ፋብሪካዉ በ390 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባና ከ130 በላይ ለሆኑ ሰራተኞች ቋሚ የስራ እድል የፈጠረ ነው ብልዋል።
ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ በመጠናቀቁ ለሌሎች ድርጅቶችም ምሣሌ ሊሆን የሚችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የግንባታ ሂደቱን በማፋጠን ዉስጥ የጎላ ሚና ለነበራቸው ሰራተኞችም ሽልማትና እዉቅና ሽልማት ተሰጥቷል።