ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት ስምምነት አደረጉ።

ስምምነቱን በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ታደሰ እና የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፈሰር ንጉሴ ደቻሳ ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ተቋማት በግብርና ምርምር ስራ፣ በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በሌሎች የግብርና ዘርፎች በትብብር ለመስራት ነው ስምምነቱን ያደረጉት።

ስምምነቱ ሳይንስን ወደ ተግባር በማዉረድ የቡና፣ የጥራጥሬ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ በእንስሳት ዘርፍ እና የሌሎች የዘርፉን ምርቶችን ምርታማነት የሚጨምርና ለዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ስምምነት የአርብቶና አርሶአደሮችን ህይወት የሚለወጥ በመሆኑ ሁለቱ ተቋማት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የስራ እድሎችን በመፍጠር፣ ለልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ በማድረግና የዉጪ ምንዛሬን በማስገኘት ለኢትዮጵያ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ግዙፍ ተቋም ነው።
በተለይም በግብርና ዘርፍ እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ገበያን ለማረጋጋት በእንስሳት ሀብት ልማት፣ በዘመናዊ ዶሮ እርባታ፣ በእንቁላልና የወተት ምርቶች፣ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በማስተዋወቅ፣በምርጥ ዘር አቅርቦት እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ በስፋት እየሰራ ይገኛል።

ሚድሮክ ለሀገር – ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY