ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በስድስት ዘርፎች ተዋቅሮ በሃገራችን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያደረገ ያለ ተቋም እንደሆነ ይታወቃል።
ከእነዚህ ስድስት ዘርፎች አንዱ አካል የሆነው የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ መሐመዲያ ቪሌጅ እና በጅማ ከተማ ለሚያስገነባቸው ሁለት ሆቴሎች ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር በፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ብራንድ የፍራንቻይዝ የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂዷል።
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት በኩል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ጀማል አህመድ እንዲሁም በማሪዮት ኢንተርናሽናል በኩል ሚስተር ካሪም ቸልቶት ፊርማቸውን አኑረዋል።
በአዲስ አበባ መሐመዲያ ቪሌጅ ላይ የሚገነባው ሆቴል፦

– የግንባታ ወጪው 2.3 ቢሊየን ብር የሚገመት ሲሆን
– ባለ 11 ወለል ህንፃ
– 250 መኝታ ክፍሎች
– የተለያዩ ስፔሻሊቲ ሬስቶራንቶች
– መዋኛ ገንዳ፣ ስፓ እና ሌሎች የመዝናኛ ፋሲሊቲዎች
የሚኖረው ይሆናል።
በጅማ ከተማ የሚገነባው ሆቴል፦
በከተማው መግቢያ ላይ በዳ ቡና በተባለውና መስህብ ባለው የተፈጥሮ ስፍራ ላይ ሲገነባ
– የግንባታ ወጪው 1.4 ቢሊየን ብር የሚገመት ሲሆን
– 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ
– የጅማን ባህልና ወግ በሚያንፀባርቅ መልኩ
የሚገነባ
– 120 የመኝታ ክፍሎች
– በአይነቱ ልዩ የሆነ ሰው ሰራሽ ሐይቅ
– የተለያዩ ዘመናዊ ሬስቶራንቶች
– የግራውንድ ቴኒስ መጫወቻ
– የመዋኛ ገንዳ እና ስፓ የሚያካትት ሆኖ ይገነባል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዚህ ቀደምም በባህርዳር እና ሐዋሳ ከተማ ላይ ለሚያስገነባቸው ሆቴሎችም ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር የፍራንቻይዝ ፊርማ መፈራረሙ ይታወሳል።
