ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ -ሚድሮክ ለሀገር
በስምምነቱ መሰረት አልኮራዬፍ ኢንዱስትሪስ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የመስኖ እርሻ ሴንተር ፒቮት ማሽኖችን በግዥ እንዲያቀርብና ለአምስት አመታት የቴክኒክ ድጋፍና ጥገና አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና በአፍሪካ የአልኮራዬፍ ኢንዱስትሪስ ሶሉሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ካሊድ ሻላባይ ተፈራርመዋል፡፡
የሚገዙ የመስኖ ልማት ሴንተር ፒቮት ማሽኖች ሚድሮክ በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በማልማት ላይ ለሚገኘዉ የቅባት እህሎች እርሻና ለሌሎች የሚያገለግሉ ይሆናሉ ፡፡
ይህም የግብርውን ዘርፍ ከማዘመን ባለፈ ምርታማነትን በመጨመር ከዘርፉ የሚገኘዉን ዉጤት የሚያሳድግ ነው ፡፡
ሚድሮክ በግብርና ዘርፍ ምርቶቹ ቡና፣ ሻይ ቅጠል፣ ቅመማቅመም፣ የሰብል፣ የአበባ፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች፣ ማር፣ ስጋና ወተት፣ ዶሮና እንቁላል እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬዎችን ለሀገር ዉስጥና ለአለም ገበያ በማቅረብ የዉጪ ምንዛሬን በማስገኘትና የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ሚናውን በመወጣት ላይ የሚገኝ ተቋም ነዉ፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ6 ዘርፎች የተደራጁ 46 ኩባንያዎችን ያቀፈና ከ80 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች በቀጥታ የሥራ እድል የፈጠረ ተቋም ነዉ።
አልኮራዬፍ ኢንዱስትሪስ በዓለም ዙሪያ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና እና የመስኖ ማሽኖችን በማምረት ይታወቃል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ -የሀገር ሀብት









