ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርጋር በመተባበር የዒድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ማዕድ አጋራ።

በማዕድ ማጋራቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ተገኝተዋል።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ እንዲሁም ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በሚደረገው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር  ካላቸው ቆርሰው ለመስጠት ለማይሳሱ ባለሀብቶች ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

በከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተደረገውን የማዕድ ማጋራት ለደገፉት ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ ጀማል አሕመድም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ነው ያሉት ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአመታዊ ትርፉ 10 በመቶውን በመመደብ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ተቋም ነው።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ተኛው የኢድ አልፈጥር በአል ከወዲሁ አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ለመግለጽ ይወዳል።

ዒድ ሙባረክ!

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY