‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር፣ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ፡፡

‎‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለማእድ መጋራቱ 10 ሚሊየን ብር ወጪ አድርጓል።

‎በዚሁ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ተገኝተዋል።

‎ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በሚደረገው በዚህ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት፤ ካላቸው ቆርሰው ለመስጠት ለማይሳሱ ባለሀብቶች ያላቸውን የከበረ ምስጋና ገልጸዋል።

‎በከንቲባ ጽሕፈት ቤት በኩል የተከናወነውን ይህን የማዕድ ማጋራት ለደገፉት ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ እና ለሌሎች ተቋማትና ባለሀብቶችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎በአጠቃላይ ዛሬ በተደረገው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ከ233 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።

‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዓመታዊ ትርፉ 10 በመቶውን በመመደብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ተቋም ነው።

‎ተቋሙ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ -የሀገር ሀብት!

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY