ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ገዛ።

ኢትዮጵያ  32ኛውን  የዓለም  የአየር ንብረት  ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ  ለተሳታፊዎች  ከሚሰራቸው ሆቴሎች አንዱ ሲሆን ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ የሚታደስ ይሆናል።

ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል።

አቶ ጀማል አሕመድ የሆቴሉን አገልግሎት በዘርፉ አለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የዋቤ ሸበሌ ሆቴል የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለትዉልድ ለማሻገር በመስማማቱ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሚድሮክ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በከፍተኛ ጥራት በመገንባት ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ዉጤት በማሳደግ ላይ የሚገኝ የሀገር ሀብት የሆነ ተቋም ነው።

ባሳለፈነው  ሳምንት  በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  የተገነባው  ደንቢ ኤኮ ሎጅ ተመርቆ ወደ ስራ  መግባቱ  ይታወሳል።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY