ይህ ፋብሪካ ወተትን ያለ ማቀዝቀዣ ለስድስት ወራት ጥራቱን ጠብቆ ማቆየት የሚችል ሲሆን፤ ለአንጋፋው ሾላ ወተት የምርት አቅም በመጨመርና ምርቶቹ በስፋት ለደንበኞች እንዲደርሱ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፋብሪካው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ወጪ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ፣ ለበርካታ ዜጎች አዲስ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ተወዳጅነት ያለውን የሾላ ወተት ተደራሽነት ወደ ክልሎች በማስፋት፣ የወተት አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ በበኩላቸው፤ ፋብሪካው የአርሶ አደሩን የድካም ውጤት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አቀናጅቶ፣ ጥራቱን የጠበቀና ታሪክ ያለውን የሾላ ወተት ምርቶችን በብዛት ለገበያ ማቅረብ ያስችላል ብለዋል።
አክለውም ከአርሶ አደሩ የሚሰበሰበውን የወተት መጠን በመጨመር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።
በተለይም በጾም ወቅት የሚገኘውን የተትረፈረፈ የወተት ምርት ብክነት እንዳያጋጥም በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት የአምራቹንና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል።
በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ጥራት ያለውን የወተት ምርት በዘላቂነት በማቅረብ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አርሶ አደሮች፤ማህበራት እና ወኪሎች የተመረጡ የወተት ላሞች ዝርያ፣ የገንዘብ ሽልማትና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
ጥራት ያላቸውን የሾላ ወተት ምርቶች፣
የወተት ምርቶች፦ ፓስቸራይዝድ ወተት፣ ኢ.ኤስ.ኤል(21 ቀን የሚቆይ) ወተት፣ ክሬም፣ የወጥና የገበታ ቅቤ
የአይብ አይነቶች፦ ጋውዳ ፣ ፕሮቮሎኖ እና ሞዘሬላ
አይስክሬም፦ በ8 የተለያዩ ጣዕሞችና በ4 የማሸጊያ መጠኖች የቀረቡ
የህጻናት ወተት ፣የተለያዩ የቺዝ ዓይነቶችን፣ለ6 ወራት ሳይበላሽ የሚቆይ ወተትን በተመጣጣኝ ዋጋ በሽያጭ ሱቆች፣ በሁሉም የኩዊንስ ሱፐርማርኬት ቅርንጫፎች እንዲሁም በአከፋፋዮቻችን አማካኝነት እስከ ደጃፍዎ እናደርሳለን።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት!










