ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቡና መቀሸሪያ ማሽኖችን ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮና ሸካ ዞኖች አበረከተ።

ማሽኖቹ የቡና አምራቾች ምርታቸውን በጥራት እንዲያመርቱ ያስችላቸዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ቡና አምራች አርሶአደሮች ማሽኖቹን በመጠቀም ቡናን ፈልፍሎ እሴት በመጨመር የበለጠ ዉጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ድጋፍ ሚድሮክ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

ተቋሙ መሰል የማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የህዝብ ሀብት መሆኑንን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑንም ተናግረዋል ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኢትዮጵያን የቡና ምርት ጥራትን በማሳደግ በአለም ገበያ ተፈላጊነቱን ከፍ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የግብርና ቢሮ ሃላፊ ዮሐንስ መላኩ ማሽኖቹ በምርት ሂደት የሚያጋጥሙ የምርት ብክነትን በመቀነስ አርሶአደሩ የልፋቱን ዉጤት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ሚድሮክ በተለያዩ ዘርፎች ለሀገር እድገት ከሚያደርገው አስተዋፅኦ በተጨማሪ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚሰራቸውን ስራዎች በማድነቅ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተመሳሳይ የቡና መቀሸሪያ ማሽኖችን ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማበርከቱ ይታወሳል።

ሚድሮክ ለሀገር – ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY