ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቡና ምርቶቹን ይዞ በቡና ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ ነው።

ሚድሮክ ሰባቱንም የቡና ምርቶቹን ይዞ ሕዳር 13 እና 14/2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የቡና ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ ነው ።

ተወደው የሚጠጡ የቡና ምርቶቹም በበቃ፣ ሊሙ፣ አየሁ፣ ገማድሮ፣ ዱየና፣ በሃ እና ሆራይዘን ናቸው።
በፌስቲቫሉ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ ዜጎች በመገኘት የሚድሮክ የቡና ምርቶችን እያጣጣሙና እየጎበኙ ነው።

የቡና አምራች ኩባንያዎች የተለያዩ ዓይነት  የቡና ምርቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ ለኤክስፖርት የተዘጋጁ የቡና ምርቶችን ጨምሮ ለእይታ ቀርበዋል፡፡

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቡና ዘርፍ በስድስት ሰፋፊ እርሻዎቹ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟሉ ምርቶች በማዘጋጀት ወደ ዉጪ ሀገራት በመላክ ለሃገራችን የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ላይ ይገኛል።

ቡናን ከማምረት በተጨማሪ የማዘጋጀትና የማከማቸት አገልግሎትም ይሰጣል። በምርትና አገልግሎቱም እንደ ሃገር በተደጋጋሚ ጊዜያት ተሸላሚ መሆኑ ይታወቃል።

ሚድሮክ ለሀገር- ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY