ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የገነባው የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ ተመረቀ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ የገነባው የአርጆ ድንጋይ ከሰል ፋብሪካ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቋል፡፡

ፋብሪካው በሰዓት 200 ቶን ታጥቦ የደረቀና ደረጃውን የጠበቀ የድንጋይ ከሰል የማምረት አቅም አለው፡፡

የድንጋይ ከሰል ምርቱ ለሲሚንቶ እና ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች እንዲሁም ለተለያዩ ሃይልን ለሚጠቅሙ ኢንዱስትሪዎች ግብአትነት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ ቀደም ሃገራችን ለዚህ ምርት ታወጣው የነበረውን የውጪ ምንዛሪ በማስቀረት ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ የጎላ ነው፡፡

የፋብሪካው መገንባት ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍትኛ የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ሚድሮክ ኢንቨስትምንት ግሩፕ ብዚህ ስፍራ ይህን ግዙፍ ፋብሪካ በመገንባቱ ምስጋናችውን አቅርበዋል፡፡

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባልስልጣናት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕን ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዱላ መኮንን አንዲሁም የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላችው አንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ሚደሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – ሚድሮክ ለሃገር

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY