ሚድሮክ ኢንቨትመንት ግሩፕ በ26 ቢሊየን ብር ወጪ በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ሊገነባ ነው።

ሚድሮክ ኢንቨትመንት ግሩፕ ፋብሪካውን ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በግልገል በለስ ከተማ መክሯል።

የሚድሮክ ኢንቨትመንት ግሩፕ ማዕድን ዘርፍ ኮርፖሬት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ሱራፌል ላቀው፥ ድርጅቱ የወርቅ ማዕድንን ዘመናዊ በሆነ መንገድ ለማውጣትና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በቡለን ወረዳ ፋብሪካውን ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ፋብሪካው ከ1 ሺህ 500 በላይ የስራ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመው፤ የፋብሪካው መገንባት በዘርፉ ያለው ሃብት እንዳይባክን እንደሚያደርግ እና ህገ-ወጥ የወርቅ ዝውውርን መልክ በማስያዝ ለሀገር ጥቅም እንዲውል እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

እንደ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገባ የክልሉ ማዕድን ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ሞርካ፥ ክልሉ የማዕድን ሃብቱን አቅም ባላቸው ኩባንያዎችና ባለሃብቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ዕውቀት በመታገዝ እንዲለማ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የፋብሪካው መገንባት የአካባቢውን ኢኮኖሚ እንደሚያነቃቃ እና እንደ ሀገር ያለውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አትንኩት ሽቱ በበኩላቸው፥ ፋብሪካው በዕቅዱ መሰረት እንዲከናወን በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY