ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ዙር የተለያዩ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ወደ ሥራ አሰማራ።

ባለሙያዎቹ በስትራክቸራል፣ በኤሌክትሪክ ዝርጋታ፣ በግንባታ ማጠናቀቅ ሥራ (Finishing) እና በመካኒክነት ሙያዎች ከተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የተወጣጡ ናቸው።
ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሥነ-ምግባርና በዘርፉ ላይ በሚያስፈልጉ የተለያዩ ቴክኒካዊ ክህሎቶች ዙሪያ ለባለሙያዎቹ ሥልጠና ሰጥቷቸዋል።
ሥልጠናውን ያጠናቀቁት ባለሙያዎች በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በመገንባት ላይ በሚገኘው ግዙፉ የመሀመዲያ ግንባታ ላይ በመሳተፍ፣ በሥልጠና ወቅት ያገኙትን ዕውቀት ከውጭ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በተግባር ያዳብራሉ።
ይህም በሀገር ደረጃ ለዘርፉ ትልቅ አቅም የሚሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።
የኮንስትራክሽን ኦፕሬሽን ኮርፖሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር ዛህራ አብዱልሃዲ በቀጣይም ሁለተኛ ዙር ሥልጠና በመስጠት፣ ሚድሮክን የሚመጥኑ ብቁ ባለሙያዎችን ለማዘጋጀትና በሂደትም ድርጅቱን ተረክበው የሚመሩ መሪዎችን ለማፍራት በትኩረት የሚሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰልጣኞቹ በበኩላቸው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሰጣቸው ሥልጠናና የሥራ ዕድል ምስጋናቸውን በማቅረብ፤ ዘርፉ የሚጠይቀውን ሙያዊ ስነ ምግባር ተከትለው በመሥራት ለሀገር ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በዘመናዊ የኮንስትራክሽን ታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የሆነው ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በዘርፉ በማስተዋወቅ፣ በኢትዮጵያ የግንባታ ዕድገት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ተወጥቷል፤ አሻራውንም አስቀምጧል።
በመንገድ፣ በሕንጻ፣ በስታዲየም ግንባታ፣ በኮንክሪት ምርትና በአስፓልት ፕላንት እንዲሁም በአሸዋ ምርት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ፣ በኢትዮጵያ የዘመናዊ ግንባታ ሂደት ውስጥ የቀዳሚነት ሚናን በመጫወት ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ፣በኮንስራክሽንና ሪል ስቴት፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በንግድና በሆስፒታሊቲ ዘርፍ በመሰማራት ከ80 ሺህ በላይ ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ተቋም ነው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት!

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY