ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በአካባቢ ጥበቃ የ”ISO 14001:2015 Environmental Management system” መስፈርቶችን በማሟላት ዓለማቀፍ የምስክር ወረቀት አገኘ።

ሚድሮክ ወርቅ የምስክር ወረቀቱን በዛሬዉ ዕለት ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (Ethiopian Conformity Assessment Enterprise Certification) ተቀብሏል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ አካል የሆነዉ ሚድሮክ ወርቅ በአካባቢ ጥበቃ የአለም አቀፍ እውቅና ያለው የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል

በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አቤል አምበርብር የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከ2001 ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ መስፈርቶች ላይ በማተኮር የምርት፣ የሲስተም፣ የስራ ላይ ደህነነትና አከባቢ ጥበቃ ላይ ጥናት በማድረግ የምስክር ወረቀት በመስጠት በኢትዮጵያ 9 ከተሞች ቅርንጫፎችን በመክፈት እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ሚድሮክ ወርቅ በአከባቢ ጥበቃ ሁሉንም አለም አቀፍ መስፈርቶች በማሟላት የምስክር ወረቀቱን በማግኘቱ እንኳን ደስ አላቸሁ ብልዋል።

የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ጋሻው ተሰፋዬም በበኩላቸው እኛ እንደ ድርጅት በደንብ ጥናት አድርገን ነዉ የምስክር ወርቀቱን የሰጠነው የሚድሮክም እድገት የማይቆም መሆኑን በመረዳት በርትቶ መስራት አለበት ብልዋል።

በተጨማሪም እውቅናው በዘርፉ ምዘና የሚያደርጉ International Accreditation Forum (IAF) እና የኬንያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ያሉ ዓለማቀፍ ድርጅቶች ጭምር ያረጋገጡት ነውም ብለዋል አቶ ጋሻው።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሀገሪቱ ቀኝ እጅ የሆነዉ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በአከባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራቸው ተግባራት ላይ ጥልቅ ጥናት በማድረግ አለም አቀፍ ምስክር ወረቀቱን በመስጠቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በሻኪሶ አከባቢ የማሕበራዊ ኃላፊቱን በከፍተኛ ሁኔታ እየተወጣ መሆኑን ገልፀው ለአብነትም ደረጃውን የጠበቀ አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ፣ የንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት፣ የትምህርት ቤት ግንባታ እንዲሁም ከ7.2 ኪሎ ሜትር በላይ የአስፓልት መንገድን በመስራት ለማህበረሰቡ ትልቅ ፋይዳ ያላቸዉን ስራዎች ማበርከቱንም አቶ ጀማል ገልፀዋል።

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY