ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ጉባዔ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል እየተካሄደ ሲሆን እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል።
በጉባኤዉ ላይ የተገኙት የማዕድን ሚንስትር ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር ) ሚድሮክ ያገኘው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ሰርተፊኬት ለኢትዮጵያ ማዕድን ዘርፍ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ የምታገኘውን ዉጤት ከማሳደግ አንፃር ትልቅ ሚና ያለዉ መሆኑን ገልፀው ለሌሎች በወርቅ ማዕድን ላይ ለተሰማሩ ተቋማት ምሳሌ ሊሆን የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል።
ምርትን መጨመርና አከባቢ ጥበቃ ላይ ትልቅ ሚና ስላለው ሁሉም ተቋማት ይህን አሰራር ተከትለው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።
የዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ፕሬዚዳንት ፖል በትማን ጉባኤው በኢትዮጵያ የተካሄደው የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያው ባስመዘገበው ዉጤት መሆኑን ገልፀዋል።
በጉባኤው የዘርፉ ተዋናዮች ልምድ ልዉዉጥ የሚያደርጉበት መድረክ መሆኑንም አንስተዋል።
ሚድሮክ ወርቅ በዕለቱ በሲያናይድ ትራንስፖርትና ማኔጅመንት ሲስተም እውቅና ተሰጥቶታል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – ሚድሮክ የሀገር












