ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ እና ፔፕሲኮ ምርቶቹን ለማምረት እና በተሻለ ሁኔታ ለገበያ መቅረብ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ተስማሙ ።

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ እና ፔፕሲኮ ያላቸውን አጋርነት እና በቅርብ ጊዜ የታዩት ለውጦችን በማስመልከት ለሚድያዎች የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ


በመግለጫው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ኃለፊ አቶ ሰዒድ መሐመድ ታዋቂዎቹ የፔፕሲኮ ምርቶች ለተወሰነ ጊዜ ከገበያ ውጪ እንደነበሩ በማስታወስ ዳግም ወደ ገበያ ለማስገባት ስራዎች መጀመራቸውን ገልፀዋል።

በሞሐ እና በፔፕሲኮ መካከል ጥልቅ ውይይት ከተደረገ በኋላ ተወዳጆቹን የፔፕሲኮ ምርቶች በተሻለ ሁኔታ ማስቀጠል የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መስማማታቸውም ተጠቁሟል።

በዚህም መሰረት ሞሐ በባለቤቱ ውሳኔ መዋቅራዊ ለውጦችን በማድረግ 45ኛ ድርጅት በመሆን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን ተቀላቅሏል።

በሚድሮክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ የሚመራው አዲሱ የሞሐ አስተዳደር ስራውን ለማስጀመር እና ምርቱን በገበያ ላይ በተሻለ ሁኔታ ለማቅረብ ለፔፕሲኮ ፕሮፖዛል አቅርቧል።

በተጨማሪም የሰው ኃይሉን በተገቢ ሁኔታ አደራጅቶ ለመምራት እና አስፈላጊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ታዋቂ የሞሐ ምርቶችን ወደ ገበያ በመመለስ ለሀገር ያለዉን ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

ሁለቱ አካላት ስምምነት ባደረጉበት ወቅት የፔፕሲኮ የምዕራብ፣ የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ቢዝነስ ዩኒት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፖል አንደርሰን ”ከሞሃ አዲስ የአስተዳደር ጋር የፔፕሲኮ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ለሚወሰዱ እርምጃዎች በመስማማታችን ደስ ብሎናል” ማለታቸውን አቶ ሰዒድ ገልፀዋል።

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ 8 ፋብሪካዎች ያለው ሲሆን ምርቶቹም ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ አፕል፣ ሚሪንዳ ኦሬንጅ፣ ሚሪንዳ ቶኒክ እና 7 ኣፕ ሲሆኑ በቅርቡ በተሟላ ሁኔታ ምርት እንደሚጀምር ተገልጿል።

በመግለጫውም ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አካልወለድ አድማሱ እና በሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ሙሄ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

እንደሚታወቀው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እንደ አዲስ ከተቋቋመ ጀምሮ ትልቅ ኪሳራ ላይ የነበሩ ድርጅቶችን ወደ ትርፋማነት እንዲሸጋገሩ በመስራት አመርቂ ዉጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

በሞሐ እየተደረገ በሚገኘው ሪፎርም የገጠሙ ችግሮችን በመፍታት ድርጅቱን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ እንደሚሰሩ ኃላፊዎቹ ገልፀዋል፡፡

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY