ሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል የፓን ኤዥያን ሬስቶራንትን አስመርቆ ስራ አስጀመረ።

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የሆቴል እና ሪዞርት ዘርፍ አካል የሆነው ሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል የፓን ኤዥያን ሬስቶራንትን ገንብቶ አገልግሎት ለመስጠት ስራ ከተጀመረ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል።
የሬስቶራንቱ መከፈት የሆቴሉ ግንባታ አካል ሆኖ ከ26 ዓመታት በፊት የባለቤቱ ክቡር ሼይኽ መሐመድ እቅድ እንደነበርም ተጠቁሟል።

ይሁን እንጂ ሆቴሉ 2013 ዓ.ም መጨረሻ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን ከመቀላቀሉ በፊት በነበረ የአመራር ችግር ምክንያት ሬስቶራንቱ ተጠናቆ ስራ ሊጀምር አልቻለም ነበር።

ከዚያ በኋላ ባሉ ጥቂት ዓመታት በተሰራ አመርቂና ውጤታማ ስራ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

ሬስቶራንቱን መርቀው የከፈቱት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ሚድሮክ ተዘግተው የነበሩ በርካታ ድርጅቶችን እየከፈተ፥ ትርፋማ በማድረግም ስኬታማ ጉዞውን ባለፉት አራት ዓመታት አረጋግጧል፤ አንዱ ደግሞ ዛሬ ስራ የምናስጀምረው ይህ ኤዥያን ሬስቶራንት ነው ብለዋል።

ክቡር ሼይኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ሸራተንን በመገንባት አዲስ አበባ ከተማ በሆቴል ዘርፍ ከመላው የዓለም ከተሞች ጋር እንድትወዳደር በማድረግ ለሀገር ያደረጉትን ታላቅ ውለታ አቶ ጀማል አስታውሰዋል።

የሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ስራ አስኪያጅ ሚስተር አንቶኒ ዋድ በበኩላቸው ጥሪ ለተደረገላቸው ክቡራን እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር የሚሰራና ከፍተኛ ጥራት ያላቸዉን አገልገሎቶች የሚሰጥ ቅንጡ ሆቴል ነው።

በሬስቶራንት መክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በኤዥያ ሀገራት ጥበበኞች ማራኪ ትርኢቶችም ቀርበው ታዳሚውን ሲያዝናኑ አምሽተዋል።

በመጨረሻም በአዲሱ ሬስቶራንት ለእንግዶች የእራት ግብዣ ተደርጎ ዝግጅቱ ተጠናቋል።

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY