ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ለተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቀረቡ።

ተቋሙ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 430 ሰራተኞቹ ለእያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር ስጦታም አበርክቷል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በስድስቱም ዘርፎቹ በ2016 በጀት ዓመት በስራቸው የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞችና አመራሮች የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

ሽልማቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ሰጥተዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በንግድና አገልግሎት፣ በኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት እና በሆቴልና ሪዞርት ዘርፎች ስር 45 ድርጅቶችን በማቀፍ ለ71 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር በሐገራችን ኢኮኖሚ ላይ የራሱን አወንታዊ አሻራ እያሳረፈ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ በቀረበው ሪፖርት መሰረት በዓመቱ የተገኘው አጠቃላይ ሽያጭም ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር በ23 በመቶ እድገት ማሳየቱ እና በበጀት ዓመቱ የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካቱም ተገለጿል፡፡

በግሩፑ ስር ያሉ ሁሉም ድርጅቶች በበጀት ዓመቱ ጥሩ አፈፃፀም እንደነበራቸውም ተገልጿል፡፡

ድርጅቶቹ እያስመዘገቡ ላሉት ከፍተኛ እድገትና እመርታ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱትና ሰራተኞች እና አመራሮች በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የእውቅና መስጠትና በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ኮከብ ሰራተኞች እና አመራሮች የሰርተፊኬት እና የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከዚህ ቀደም በ2013 ፣2014 እና 2015 ለሶስት ተከታታይ አመታት የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር አድርጓል፡፡

የዘንድሮውን የእውቅና መርሀ-ግብር ልዩ የሚያደርገው ሁሉም የ6ቱም ዘርፎች ሰራተኞችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ በዓሉ እንዲዘጋጅ የተደረገው ሰራተኛው እርስ በእርሱ እንዲተዋወቁ ነው፡፡

በተጨማሪም ይህ አይነቱ የእውቅና እና የሽልማት ዝግጅት ቀጣይነት ያለው እንደሆነ በማንሳት ድርጅቶች እርስ በእርስ በቀና መንፈስ በመወዳደር ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉና በመደጋገፍ አብረው እንዲሰሩ ለማስቻል ነው።

በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የእውቅና እና የሽልማት መርሃ ግብር ላይ ከ6500 በላይ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በላቀ አፈፃፀም ትርፍ ያስመዘገቡ ድርጅቶችም ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድን ጨምሮ የየዘርፎቹ ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY