በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኘው አዲስ ፓርክ እና ማኔጅመንት በተለምዶ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተባለ የሚጠራው በአዲስ መልክ ግንባታው ተጀምሯል።

ባለፉት 18 ዓመታት በኢትዮጵያ ግዙፍ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች ሲያስተናግድ የቆየው ሚሊኒየም አዳራሽ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልኩ ተገንብቶና የማስፋፊያ ስራ ተደርጎለት በአጭር ጊዜ ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናል።

ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮግራሞች፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ሀይማኖታዊ ፕሮግራሞች፣ ምርቃቶች እንዲሁም በሌሎች ፕሮግራሞች ላይ ሚሊኒየም አዳራሽ ትልቅ ሚና ሲጫወት የቆየ ነው።

የአዳራሹ እድሳቱና የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በዋናነት ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) ዝግጅት አካል ሲሆን፣ በቦታው ላይ Moxy by Marriott የተሰኘ ግዙፍና ዘመናዊ ሆቴል ይገነባል።

ሰፊ የመኪና ማቆሚያ፣ የላቀ ቴክኖሎጂ ያካተተ ሲሆን፣ የአዳራሹን የማስተናገድ አቅም እና ዘመናዊነት ይበልጥ በማሳደግ ተጨማሪ አገልግሎት እንዲሰጥ ሆኖ ይገነባል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለ32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተሳታፊዎች የሚሆኑ በሚሊኒየም አደራሽ የሚገነባውን ሆቴል ጨምሮ 1,500 አልጋዎችን የያዙ አምስት ዘመናዊ ሆቴሎችን በአዲስ አበባ ለመገንባት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ እጅግ ዘመናዊ የሆነና የሸራተን አዲስ ሆቴልን ስያሜ የሚይዝ ሌላ ሆቴል ይገነባል። በመሀመድያ የመኖሪያ መንደር (Four Points by Sheraton) ሆቴል ግንባታው ተጀምሯል።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY