ፋብሪካዉ የዉጪ ምንዛሬን በማዳን ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን ለአካባቢው ማህበረሰብም ተጨማሪ የስራ እድል ይፈጥራል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ሚድሮክ መሰል አዳዲስ ፋብሪካዎችን በመክፈት ሀገር በቀል የኢኮኖሚክ ሪፎርምን በማሳካት የወጪ ገቢ ምርቶችን በመተካት ፈር ቀዳጅ በመሆን ተምሳሌትነቱን እንደሚቀጥል ገለፀዋል። ሚድሮክ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በንግድ፣ በሆቴልና ሪዞርቶች እንዲሁም በኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፎች አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ በመገንባት ወደ ስራ እያስገባ እንደሆነም ጠቁመዋል።


የኮምቦልቻ የብረታ ብረት ምርቶች ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢቂላ በቃና በበኩላቸው ዛሬ የተመረቀው ፋብሪካ 30 የበር አማራጮችና 20 የቀለም አማራጮች ያለዉ መሆኑን ገለፀዋል። የሸገር ከተማ አሰተዳደር ም/ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አሰተባባሪ አቶ ጉዮ ገልገሎ ኮምቦልቻ የብረታ ብረት ምርቶች ኢንዱስትሪ ማህበራዊ ኃላፊነት በመወጣት የሚታወቅ እንደሆነ ገለፀው ዛሬ የተመረቀው ፋብሪካ የዉጪ ምንዛሬን የሚያድን መሆኑን ተናግረዋል።










