በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተገነባው የሱልጣን አሊሚራህ ሃንፍሬ  መስጂድ ተመረቀ።

መስጠት አያጎድልም -ሚድሮክ ለሀገር-ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተገነባው የሱልጣን አሊሚራህ ሃንፍሬ  መስጂድ ተመረቀ።

ግንባታዉ ተጀምሮ ለ30 አመታት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ባማረ መልኩ ተጠናቆ አገልግሎት መሰጠት ጀምሯል።

መስጅዱ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዉሲ-ሪሱ መስተዳድር አይሳኢታ ከተማ ይገኛል።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኢትዮጵያ እድገት ለማረጋገጥ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከመስጂድ ግንባታው በተጨማሪ በክልሉ በርካታ የኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ሰፊ የስራ እድሎችን እየፈጠረ መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ ሀጂ አወል አርባ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀ-መንበር ሼይኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድን አመስግነዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተለያዩ ሰዉ ተኮር ስራዎች ላይ በመሳተፍ የዜጎቻችን ኑሮ ለማሻሻል እየሰራ ነዉ ብለዋል።

ሚድሮክ ኢንቨሰትመንት ግሩፕ የሱልጣን ዓሊሚራህ ሃንፍሬን ቤተመንግሥት ገንብቶ እንደሚያስረክብም ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ጀማል አህመድ ተናግረዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከትርፉ 10 በመቶውን ለተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነት በመመደብ ሀገራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ የሀገር ሀብት የሆነ ተቋም ነው።

ሚድሮክ ለሀገር-ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY