በሚድሮክ እንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ በጅማ አከባቢ የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ/ተ/ግ/ማ ሰራተኞች ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት እና ለግብርና ዘርፉ የሽልማት እና እዉቅና መሰጠት ፕሮግራም አካሄዱ።

በጅማ አከባቢ የሚገኙት የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማ ሰራተኞች ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና የግብርና ዘርፍ እያደረገላቸው በሚገኘው ሁለንተናዊ ድጋፍ እና በባለቤትነት ስሜት ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ ስላስቻላቸው በመደሰታቸውና ይህም ሁኔታ ቀጣይነት እንዲኖረው በማሰብ ሽልማታቸዉን ለዘረፉ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ለአቶ ፈለቀ ታደሰ እና ለሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ዋና ስራ አስኪያጅ ለአቶ ነፃነት ጋሻዬ ሰጥተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ፈለቀ ታደሰ ባደረጉት ንግግር የቡና ምርትን በመጨመር ደረጃውን የጠበቀ ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ የድርጅቱን ገቢ ለማሳደግ እና የሀገርን ኤኮኖሚያዊ ፈይዳን ለማስጠበቅ በርትተው መሰራት እንዳላባቸውና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና በስሩ የሚገኙት ድርጅቶች ሁሉ የሰራተኛው እንደሆኑና ሰራተኛው አሁንም በፍፁም የባለቤትነት ስሜት መስራት እንደሚያስፈልግና አመራሩም ሁሌም ከሰራተኛው ጎን መሆኑን በማንሳት ፕሮግራሙንና ሽልማቱን ያዘጋጁ አካላትን አመስግነዋል።


የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ነፃነት ጋሻዬም በበኩላቸው ያለሰራተኞች ድርጅትን ማሰብ አይቻልም ሰራተኛው በስራዉ ደስተኛ መሆን ሲችል ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል በማመን የደሞዝ ጭማሪ እንደተደረገ በመግለፅ የተሻለ ወጤት ለማምጣት በርትተው መስራት እንደለባቸው ተናግረዋል።
የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ምክትል ስራ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ቁምላቸው ሰራተኞች ያለ ድርጅት ድርጅቱም ያለ ሰራተኞች ዉጤታማ መሆን ስለማይችሉ የቡና ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ጅማ አከባቢ የሚገኙ የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ሰራተኞች በርትተው መስራት እንዳለባቸው መልከት አስተላልፈዋል።
ሽልማቱን ያዘጋጁት ሰራተኞች ተወካዮች በበኩላቸው የሽልማት እና እዉቅና መሰጠት ፕሮግራሙን ያዘጋጁት የተደረገላቸውን የደሞዝ ማሻሻያ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት እያደረገላቸው ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ በማስመልከት እንደሆነ የገለፁ ሲሆን የስራ ኃላፊዎች ከሰራተኞች ጋር ተናበው መስራት ሲችሉ ሰራተኞች ስራቸውን በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ከፍተኛ ዉጤት ለማስመዘገብ እንደሚያስችል ገልፀዋል።
በተጨማሪም ሰራተኞቹ ይህ ተሞክሮ ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆን አርአያነት እንደሆነ ጠቁመዋል ።

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE