የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በ2010 ዓ.ም. ከአከባቢ ማህበረሰብ በተነሳ ጥያቄ መሠረት ለሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ማምረት ያቆመ ሲሆን ከማህበረሰቡ ጋር በመወያየት ከስምምነት ከተደረሰ ቦኃላ የምርት ማምርት ሂደቱን ጥር 1፣ 2013 ዓ.ም. እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡
የካቲት 19 ቀን 2014ዓ.ም. የጉጂ ዞን አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በአካባቢዉ ባህል መሰረት የምስጋናና የምርቃት ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡
በዚህ የምስጋናና የምርቃት ፕሮግራም ላይ ሚድሮክ ወርቅ ስራ ባቋረጠበት ጊዜ የአካባቢዉ ህብረተሰብ የኩባንያዉን ንብረት ከመጠበቅ በተጨማሪ ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን በጋራ ሆነዉ በመፍታት ኩባንያዉ ወደ ሥራ እንዲገባ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት አመስግነዋል፡፡
የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ. የተ. የግ. ማ. የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን በኩባንያዉ አመራሮች ቁርጠኝነት በብዙ ሚሊዮን ብር የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄ የመመለስ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአዋጅ የተቀመጠዉን ከሽያጭ የሚገኘዉ የሮያልቲ ክፍያ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሠረት እየተከናወነ ሲሆን ወረዳዉም ያሉበትን የልማት ጥያቄ በቅደም ተከተል ለመመለስ ዕቅድ አዘጋጅቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY