
ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በ2010 ዓ.ም. ከአከባቢ ማህበረሰብ በተነሳ ጥያቄ መሠረት ለሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ማምረት ያቆመ ሲሆን ከማህበረሰቡ ጋር በመወያየት ከስምምነት ከተደረሰ ቦኃላ የምርት ማምርት ሂደቱን ጥር 1፣ 2013 ዓ.ም. እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡ ቀደም ሲል ያለምንም ስልጠናና በቂ ሞያዊ ዝግጅት በልምድ ይሰሩ የነበሩ ስራዎች አሁን አሁን ከጊዜዉ መዘመን ጋር ተዳምሮ አስፈላጊዉን ትኩረት በማግኘት ላይ ናቸዉ። ለምሳሌ በጥበቃና በተቋማት ደህንነት ዘርፍ በሀገራችን በርካታ ድርጅቶች ህጋዊ እዉቅና እየተሰጣቸዉ አስፈላጊዉን የሰዉ ሃይል እየመለመሉና እያሰለጠኑ አገልግሎቱን ለተለያዩ ተቋ ማት የሚሰጡበት ሁኔታ የተለመደ አሰራር እየሆነ መቷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል.ማ. ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በራሱ የመለመላቸዉን 420 የጥበቃ ባለሞያዎች ከጥቅምት 2014 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ ለአንድ ወር በሁለት ዙር አሰልጥናቸዉን ሰልጣኞች በሰርተፍኬት አስመርቋል። የኩባንያዉን የጥበቃ ስራ ማዘመንና አስተማማኝ ማድረግን አላማዉ ያደረገዉ ይህ ስልጠና ከሌሎች አካባቢዎችና ከሻክሾ ወረዳ ለተዉጣጡ የስራ እድልን ከመፍጠር በለፈ የአካባቢዉን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የበኩሉን አስተዋፅኦ እነደሚያደርግ ነዋሪዎች እመነታቸዉን ገልፀዋል።
ሰልጣኞቹ የዘርፉ ሞያተኛ የሚያደርጋቸዉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ና የሚድሮክ እንቨስትመንት ግሩፕ ሰረተፍኬት ያገኙት ባጠቃላይ እያንዳንዳቸዉ የ 145 ሰዓታት የንድፈሀሳብና የተግባር ስልጠና አግኝተዉ የተሰጣቸዉንም ምዜና በአግባቡ ማለፍ በመቻላቸዉ ነዉ።
ተመራቂዎቹ በቆይታቸዉ ከወሰዱአቸዉ ስልጠናዎች መካከልም የጥበቃ ሰራተኞች ስነ ምግባር ፣ ህገ—መንግስትና የህግ የበላይነት፣ ወንጀል መከላከልና ምርመራ ፣ የኩባንያ ጥበቃና የፍተሻ ስልቶቸ ፣ የመሳሪያ አጠቃቀም ፣ ሚሊቴሪ ስትራቴጅና የአካል ብቃት ይገኙበታል።