ላለፉት ዓመታት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በዘርፉ በማስተዋወቅ፣ በኢትዮጵያ የግንባታ ዕድገት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ተወጥቷል፤ አሻራውንም አስቀምጧል!
በመንገድ፣ በሕንጻ፣ በስታዲየም ግንባታ፣ በኮንክሪት ምርትና በአስፓልት ፕላንት እንዲሁም በአሸዋ ምርት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ፣ በኢትዮጵያ የዘመናዊ ግንባታ ሂደት ውስጥ የቀዳሚነት ሚናን በመጫወት ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ከተገነቡት ግዙፍ ግንባታዎች ጀርባ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ አለ። የተቀናጀ የአመራር ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ አርአያ የሆነው ሚድሮክ ኮንስትራክሽን፣ በአሁኑ ወቅትም ግዙፍ ግንባታዎችን እያከናወነ ይገኛል።
የ15 ሕንጻዎችን፣ የአንድ መንገድ፣ የአንድ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የሁለት ስታዲየሞችን እንዲሁም በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ስድስት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ግንባታ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ 24 ሰዓት እየተሰራ ነው።
የሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ አመራሮችና ባልደረቦች ያለፉትን ስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን በጋራ ገምግመዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች ባለፉት ስምንት ወራት ያከናወኗቸውን ተግባራት በጥሩ ሁኔታ ገምግመው፣ በቀሪ ወራት ከዚህ በበለጠ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ በርሄ ለተገኘው ስኬት ባልደረቦቻቸውን አመስግነው፣ በቀጣይ ከዚህ በበለጠ በርትተው እንዲሠሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚን ወክለው ንግግር ያደረጉት ኮንስትራክሽን ኦፕሬሽን ኮርፖሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር ዛህራ አብዱልሃዲ ዘርፉ ለድርጅቱ ስኬት የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት!










