በውቢቷ ባህር ዳር የፎር ፖይንት ባይ ሸራተን ጣና ሆቴል መገንባት የከተማዋን ውበት ይበልጥ ያጎላል” አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በባህር ዳር ከተማ የፎር ፖይንት ባይ ሸራተን ጣና ሆቴልን ግንባታ በይፋ አስጀምሯል።

የግንባታ መርሃ ግብሩን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ በጋራ አስጀምረዋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሆቴሉ ተፈጥሮ ለከተማዋ የለገሳትን ጸጋ አጉልቶ ለማሳየት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው፣ ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለሥራ እንዲበቃ አሳስበዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአቶ ጀማል አሕመድ መመራት ከጀመረ ወዲህ ውጤታማነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ለዜጎች አለኝታ በመሆን ላይ ይገኛል” ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ግሩፑ ለሀገር እድገት በሁሉም ዘርፍ በሚደረጉ ጥረቶች ግንባር ቀደም በመሆንና በችግር ጊዜም ፈጥኖ በመድረስ ለሚያበረክተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ በበኩላቸው፤ የሆቴሉ ግንባታ በ18 ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ገልጸዋል።

ሚድሮክ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያስተዳድራቸው ዘመናዊ ሆቴሎች በተጨማሪ፣ በአሁኑ ወቅት በጅማና በሐዋሳ ከተሞች የፎር ፖይንት ባይ ሸራተን ሆቴሎችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ግሩፑ የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግና የዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን ፍላጎት የሚያሟሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በባህር ዳር ከተማ የሚገኘው ጣና ሆቴል ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን የተቀላቀለው በሐምሌ ወር 2001 ዓ.ም ነበር።

ቀደም ሲል 64 አልጋዎች ብቻ የነበሩት ይህ ሆቴል፣ በአዲስ መልክ ሲገነባ 120 አልጋዎች ይኖሩታል፡፡

ለሆቴሉ ግንባታ ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቧል። ግንባታዉን ደግሞ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ያከናውናል።

ሁልጊዜም መርሁን “ለሀገር” አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ይህን ዘመናዊ ሆቴል በባህር ዳር በመገንባቱ ትልቅ ኩራት ይሰማዋል።

በአሁኑ ወቅት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ45 በላይ ኩባንያዎችን በሥሩ አቅፎ የያዘ ሲሆን፣ ከ80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት!

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY