ታላቁ ክለብ ባለታሪኩ የአርበኝነት ማሳያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዛሬ ደምቆ ውሏል።

90 አመታትን በስኬትና በፈተና የመጣው አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ከዛሬ ጀምሮ ትኩረቱን ወደ ከፍታ ማማ ለማድረግ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል።

ሁሉም በአንድ ድምጽ ስለጊዮርጊስ በመከረበት በዚህ መድረክ አንጋፋውን ክለብ በቀጣይ መሰረት ይዞ እንዲጓዝ የሚያግዙና የሚሰሩ አመራሮችን ሰይሟል።

ክለቡ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ከክለቡ አጋር ድርጅቶች ማለትም ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ከዳሸን ባንክ፣ ከሞሃ ፔፕሲ፣ ከቢጂአይ (BGI) ከቀድሞ የክለቡ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበርና ከክለቡ ደጋፊዎች የተወጣጡ ዘጠኝ ጊዜያዊ የቦርድ አባላትን የክለቡ አመራርና ደጋፊዎች በሙሉ ድምፅ አጽድቀውታል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ክለቡ ከነበረበት ችግር እንዲወጣ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሚያደርገው ድጋፍ ታላቅ ምስጋና አቅርበው፣ የከተማ መስተዳደሩም ለክለቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ በበኩላቸው ክለቡ ከሁላችንም የግል ፍላጎት በላይ በመሆኑ ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በመተው፣ ወደነበረበት ገናናነት በመመለስ ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል።

ዛሬ የተመረጡት የቦርድ አባላት እስከ ጥቅምት ወር /2019 ዓ.ም የክለቡን ሀብትና ዕዳዎች በመለየት፣ የመተዳደሪያ ደንቦችን በማዘጋጀት፣ የስፖርት ክለቡን ማኅበራት በማደራጀትና ሌሎች ለክለቡ ጠንካራ መሠረት የሚሆኑ ሥራዎችን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት በማከናወን ክለቡን ለመታደግ መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ስፖርት ክለቡ በዓለማችን ደግ ሰው ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ስለሚወደድና ስለሚደገፍ ዕድለኛ መሆኑን ገልጸው ለክለቡ የሚጠቅሙ ሀብቶችና ሐሳቦችን ማምጣት የሁላችንም ኃላፊነት በመሆኑ፣ በተለይም ደጋፊዎች አንድነታቸዉን ለማሳየት መሰለፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሚድሮክ ክለቡ ያጋጠመውን የፋይናንስ ቀውስ ለመፍታት የገንዘብ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ አዲስ ያስፈረማቸውን አራት ተጫዋቾች ሙሉ ወጪ በመሸፈንና የቀድሞውን የክለቡን አሰልጣኝ “ሚቾን” በመመለስ የምንጊዜም አጋርነቱን በተግባር ማሳየቱን ጠቁመው፣ ድጋፉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ልዩ ሥፍራ የሚሰጠው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በልዩ ልዩ አስተዳደራዊ ችግሮች ተብትቦ ሕመሙ ሲፀና ዝም ብሎ የመመልከት ድፍረትን ያላገኙት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ከልጅነታቸው ጀምረው የሚደግፉትን ክለብ ለመታደግ ዛሬ ትልቅ አሻራ አስቀምጠዋል፣ ለዚህ ስራቸውም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በአለም ላይ በለጋስነታቸው በሚታወቁት በሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ የበላይ ጠባቂነት የሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የቁርጥ ቀን ልጅ በሆነው በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ አማካኝነት አንጋፋው ክለብ የከፍታ ጉዞውን ዛሬ ባበሰረበት መድረክ የክለቡ ወዳጆችና ደጋፊዎች ደስታ ፍጸም የተለየ ነበር።

90 አመታትን ያስቆጠረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዛሬ ከክለብም በላይ ሆኖ ሰለ ሰላም ስለ አንድነት በጋራ በአንድ ድምጽ ተዘምሮለታል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY