አለም አቀፍ አስተርኖሚካል ህብረት ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲንን የክብር አባል አደረገ

አለም አቀፍ አስተርኖሚካል ህብረት ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲንን የክብር አባል አደረገ

***********************************

ዓለም አቀፉ አስትሮኖሚካል ህብረት ሼህ መሐመድ አላሙዲን ለኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥቷቸዋል።

ህብረቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ላለፉት 15 ቀናት ጠቅላላ ጉባዔውን ሲያካሂድ ቆይቷል።

በየሦስት ዓመቱ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ በዘንድሮው ጉባኤው ላይ ከ3200 በላይ የምርምር ውጤቶች የቀረቡበት እና በአካል እና በበየነ መረብ የዓለም ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

ህብረቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት በሶስት አመት አንዴ ዕውቅና ይሰጣል፡፡

በዚህ መሰረት በዘንድሮው ጉባዔ ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲን ከአውሮፓውያኑ 2004 ጀምረው ለኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ እድገት ላደረጉት አስተዋጽኦ የክብር አባል እንዲሆኑ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲን በኢትዮጵያ የህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ህብረቱ የክብር አባል እንዲሆኑ ዕውቅና የሰጣቸው፡፡

የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ የስልጠና እና ምርምር ማዕከል ሲቋቋም ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲን ከፍተኛውን አበርክቶ ማድረጋቸው ይታወሳል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ለህዋ ሳይንስ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ላባረከቱት አቶ ተፈራ ዋልዋ በአውሮፓውያኑ 2018 ቪዬና በተካሄደው ጉባኤ ዓለም አቀፉ አስትሮኖሚካል ህብረት እውቅና ሰጥቷቸዋል።

አለም አቀፉ አስተርኖሚካል ህብረት በአውሮፓውያኑ 1919 የተመሰረተ ሲሆን አለም አቀፍ ህዋ እና ጠፈር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ የሚወስን ከ85 አገራት በላይ እና ከ12 ሺህ በላይ ሳይንቲስቶችን በአባልነት ያቀፈ ነው፡፡

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY