አንድ ሰው ብዛቱ ስንት ነው?

እኝህ ሰው ከአርባ አምስት በላይ ግዙፍ ተቋማትን በአንድ ጊዜ ይመራሉ፡፡ ከሰማኒያ ሺህ የሚልቁ ሰራተኞችን ያስተባብራሉ፡፡ እንዲህም ሆኖ ስለ ሥራቸው እንጂ ስለ ራሳቸው ሲያወሩ መስማት ብርቅ ነው፡፡ የሚያውቋቸው ስትራቴጂካዊ የተቋም መሪ፣ መዋቅራዊ የለውጥ ማኅንዲስና ለተጨማሪ ስኬት ሁሌም የሚተጉ ሲሉ ይገልጿቸዋል፡፡
የቅርብ ወዳጆቻቸው ደግሞ ስማቸውን ጠርተው “አንድ ሰው ብዛቱ ስንት ነው?” ብለን የምንጠይቀው እሱን ስናይ ነው ሲሉ ያወድሷቸዋል፡፡
በርግጥም ጀማል አህመድ የሚለው መጠሪያ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ሰማይ ላይ የሚያበራ ኮከብ ሆኗል፡፡ ነገራችን ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆን ጥቂት ማስረጃዎችን እንደርድር፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ጉልህ ሃገራዊ አሻራን አኑሯል፡፡ ይህም ሆኖ ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረበት ሁኔታ ተቋማዊ መፋዘዝ የሚታይበት መሆኑ የሚያከራክር አልነበረም፡፡
ስለዚህም የሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ ባለቤት ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲና አመራራቸው ሃገራዊውን ተቋም ከገባበት መቀዛቀዝ የሚወጣ ብሎም ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚያሸጋግር ሥራ አስፈፃሚን ለወንበሩ ማጨት ነበረባቸው፡፡
ብዙ ማውጣት ማውረድ ያስፈለጋቸው አይመስልም፡፡ የቀደመ የስኬት ታሪካቸው ለዛ ትልቅ ኃላፊነት የሚያበቃቸው ሰው እዛው ሚድሮክ ውስጥ ነበሩ፡፡ አላመነቱም ዕድሉን ሰጧቸው፡፡
እርሳቸውም አላሳፈሯቸውም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊታሰብ የማይችልን ለውጥ አምጥተው አስመለከቷቸው፡፡
አቶ ጀማል የተዋጣላቸው ስትራቴጂካዊ የተቋም መሪ ናቸው፡፡ እማኝ ለማግኝት ብዙ አንደክምም፡፡ የሚመሩትን ግዙፍ ተቋም ያለፉት ዓመታት ስኬት ብቻ እንመልከት፡፡ በቀደመው ዘመን “ሚድሮክ በተበታተነ መልኩ ይንቀሳቀስ የነበረው ተቋም ወደ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተሸጋገረው በእርሳቸው የመሪነት ጥበብ ነው፡፡
ይህ ለውጥ ተራ የመጠሪያ ሽግግር አይደለም፡፡ ይልቁኑስ በተጠና መዋቅራዊ ማሻሻያና አንድ ሚድሮክ በሚል መሪ ቃል ግዙፉን ተቋም ለትልቅ ስኬት ያበቃ እንጂ፡፡
በተበታተነ መንገድ የነበሩ ድርጅቶችን ወደ አንድነት ያመጣው ይህ የአመራር ፍልስፍና ተቋሙ ሀብቱን በአግባቡ እንዲጠቀምና ወጭውን እንዲቀንስ በማስቻል በኩልም ወደር የሌለውን ሚና ተጫውቷል፡፡
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጀማል አህመድ ከስትራቲጅካዊ መሪነታቸው ባለፈ ስልታዊ መዋቅራዊ ሽግግርን በመፍጠርና ዘመኑን የዋጀ ተወዳዳሪ የንግድ ተቋምን በማደራጀት በኩልም በአገራችን ስማቸው ከፊት የሚጠቀሱ ግለሰብ ናቸው፡፡
እዚህ ላይ ከ45 በላይ ግዙፍ ተቋማትን በበላይነት በመምራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ያስቻሉበትን ጥበብ አለማድነቅ ንፉግነት ይሆናል፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ ከምስረታው አንስቶ በየዘመናቱ የተለያዩ ተግዳሮቶችን ሲያልፍ ቆይቷል፡፡ ይህም ሆኖ በአገር አቀፍም ሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የነበሩ ፈተናዎችን ከቀደመው ላቅ ያሉ መሆናቸው የሚያከራክር አይደለም፡፡
በመሆኑም በመላው ዓለም የግዙፍ ኮርፖሬት ተቋማት መሪዎች እየተፈተኑ ባሉበት በዚህ ወቅት ማዕበሉን ሊያሻግር የሚችል በሳልና ቆራጥ መሪን ማግኘት መታደል ነው፡፡
አቶ ጀማል አህመድ ኮቪድ የመላው ዓለም ስጋት ሆኖ ከሰው እኩል የንግድ ድርጅቶችን ሕልውና በተገዳደረበት ዘመን የሚመሩትን ግዙፍ ተቋም ሰራተኞች ደኅነነት አስጥብቀው የድርጅቶቻቸውን ስኬት ያስቀጠሉበት መንገድ አስደናቂ ነበር፡፡
እዚህ ላይ ሌላም ነገር መጨመር ሳይኖርብን አይቀረም፡፡ እርሱም ሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ ከንግድ ተቋምነት ባለፈ ወደ ላቀ አምራችነትና የተሳካ የውጭ ንግድ ዘርፍ ተሳትፎ የገባበት ሒደት ነው፡፡
ተቋሙ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባካሔደው ማሻሻያ በማዕድንና ግብርና ዘርፍ የውጭ ንግድ ተሳትፎ ጉልህ እምርታን አምጥቷል፡፡ ይህም የአገርን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሻሻል በኩል የማይናቅ አስተዋጽዖን አድርጓል፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የአገር ግዙፍ ሀብት እንደመሆኑ መጠን መሪ ቃሉም “ለሃገር” የሚል ነው፡፡ አቶ ጀማል አህመድም ቢሯቸው ተቀምጠው ወንበር ከማሞቅ ይልቅ የሚመሯቸው ተቋማት ወዳሉባቸው ስፍራዎች ባስቸጋሪ ሁኔታዎችውም ውስጥ ሳይቀር በማቅናት ለተቋማቸውና አገራቸው ዕድገት ደከምኝ የማያውቁ ቆራጥ መሪ ናቸው፡፡
ለዚህም ይመስላል ከሚመሩት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃላፊነት ጎን ለጎን የኢትዮጵያ አገር አቀፍ የዘርፍ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የመሆንን ሀሳብ የተቀበሉት፡፡
አቶ ጀማል በተግባር የተፈተነ የአመራርነት ጥበብ ያላቸው እንደመሆኑ መጠን አዲሱ ኃላፊነታቸው ተቋማዊ ስኬታቸውን በሃገር አቀፍ ደረጃ እንዲደግሙ ሰፊ መደላድልን የሚፈጥር ነው፡፡
ይህም ምክር ቤቱ ተቋማዊ መዋቅራዊ ማሻሻያን በማድረግ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚታይና ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ ሚናን እንዲጫወት ያግዛል፡፡
ቁጥብ ግን ደግሞ ደፋር የሚባሉት የአቶ ጀማል አህመድ የዘርፍ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት መሆን የንግዱን ማኅበረሰብ ድምጽ በማሰማትና በኢኮኖሚው ውስጥ ሳንካ የሆኑ ችግሮችን በመፍታት በኩልም አዲስ ተስፋን የሰነቀ ተደርጎ ተቆጥሯል፡፡
መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ!
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሃገር ሀብት

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY