‎ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹና ብዙ ዕድሎች ያሏትና ዉጤታማ መሆን የሚቻልባት ሀገር መሆኗን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ገለፁ።


ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህንን ያሉት ዛሬ በተጀመረው ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ 2026 ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ነው።

‎አቶ ጀማል አሕመድ ሚድሮክ ላለፉት 30 አመታት በኢትዮጵያ የተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች ላይ በመሰማራት ለሀገር እድገት ከፍተኛ አሰተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ለፎረሙ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

‎ከሀገር በቀል ኢኮኖሚክ ማሻሻያ በኋላ የሚድሮክ ትርፍ እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹና ዘርፍ ብዙ ዕድሎች ያሏት በመሆኗ ቢሰራበት ዉጤታማ መሆን የሚቻልበት ሀገር ናት ለዚህም በስድስት የተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማራው ሚድሮክ ማሳያ ነው ብለዋል።

‎አራተኛው ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ 2026 ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፎረም ‹‹ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ዝግጁ ናት›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 17 እና 18/2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡

‎በፎረሙ ላይ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምርቶችና አገልግሎቶች ለእይታ ቀርቧል።

ሚድሮክ ከ80ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በቀጥታ የስራ እድል ፈጥሯል።
‎‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY