ኢትዮ አግሪ ሴፍት የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜትና ንግድ ስምምነት “ዛም ሲድ” ከተባለ ድርጅት ጋር ተፈራረመ::ስምምነቱ አህጉራዊ የንግድ ትስስርን ከማጠናከር ባሻገር በዘርፉ ውጤታማ አስተዋፅኦ ለማበርከት ታላቅ ፋይዳ ያለው ተግባር ነው ተብሏል፡፡

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ግብርና ዘርፍ አካል የሆነው ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማ መቀመጫውን ዛምቢያ ሃገር ካደረገው “ዛም ሲድ” የተባለ ዓለም አቀፍ የዘር ንግድ ኩባንያ ጋር በሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ስምምነቱን ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱም ኢትዮ አግሪ ሴፍት የድቃይ በቆሎ ዝርያ ምርጥ ዘር አምርቶ ለኢትዮጵያ የበቆሎ አምራች አርሶ አደሮች ማቅረብ የሚያስችል ነው፡፡

ስምምነቱን የኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማ ዋና ስራ አስኪያጅ ባህሪው ሰመረ እና የ“ዛም ሲድ” ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቭ ክሌመንት ፈርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ኢትዮ አግሪ ሴፍት በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት በኩል አስፈትሾ ከመረጠው እና ለዝርያ አፅዳቂ ኮሚቴ ካቀረባቸው የዛምሲድ ድቃይ የበቆሎ ዝርያዎች መካከል አንዱን (ZMS721) በኢትዮጵያ አምርቶ ለመሸጥ ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ማረጋገጫ ካገኘ በኋላ ነው፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ታደሰ “ይህ ቀን ለእኛ ልዩ ቀን ነው እንደ ድርጅት ብቻም ሳይሆን እንደ ሃገር የተዳቀለ የበቆሎ የዘር ብዜቶችን ለሃገራችን አምራች ገበሬዎች ለማቅረብም የሚያስችለን በመሆኑ ደስተኞች ነን” ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ የድርጅታችን ባለቤትና ሊቀመንበር ሼይኅ መሐመድ አላሙዲን ራዕይና ፍላጎት ከማሳካት አንፃር ፋይዳው ጉልህ መሆኑን አቶ ፈለቀ ገልፀዋል፡፡

የ“ዛም ሲድ” ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቭ ክሌመንት በበኩላቸው “ይህ ስምምነት የተፈፀመው አፍሪካዊ በሆኑ ሁለት ድርጅቶች መካከል በመሆኑ እንደ አህጉርም ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ዋና ስራ አስፈፃሚው የኢትዮጵያ ገበሬዎች ከዚህ ስምምነት ከፍተኛ ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ አምናለሁ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አቶ ባህሪው ሰመረ የኢትዮ አግሪ ሴፍት ዋና ስራ አስኪያጅ “ይህ ለእኛ ትልቅ ትርጉም ያለውና በሃገራችን የግብርና እድገት ላይ የራሱን አስተዋፅዖ የሚያሳርፍ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ3.4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ የሚሸፈን ሲሆን ይህ ስምምነት ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ከሚያመጣው ተጨማሪ ትርፍ በዘለለ በሃገሪቱ የበቆሎ ዘር አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ ከፍተኛ የሆነ አወንታዊ አስተዋፅዖ ይኖረዋል፡፡

ስምምነቱም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚፀና ሲሆን እነደ አስፈላጊነቱም በሁለትዮሽ ስምምነት የሚታደስ ይሆናል፡፡

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY