ኤች ዜድ ቡና ላኪ ኃ/የተ/ግ/ ማህበርለቡና አምራችና አቅራቢዎች የእዉቅና ሽልማት ሰጠ።

እዉቅናና ሽልማቱ በ2016 እና 2017 ዓ.ም በጀት አመት የቡና ምርትን በብዛትና በጥራት በማቅረባቸው የተሰጣቸው ሲሆን ከአቶ ፈለቀ ታደሰ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ እጅ ተቀብለዋል።

ማህበሩ ከሁለት የሲዳማ ክልል ወረዳዎች (ሸበዲኖ እና ዳሌ) ለተወጣጡ 486 ቡና አምራች ገበሬዎች የእዉቅና ምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

በዘመኑ የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው 6 ቡና አቅራቢዎች ከብር 150,000 እስከ 300,000 ሽልሟል።

አቶ ፈለቀ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር የቡና ምርታማነትና ጥራትን በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኘውን የዉጪ ምንዛሬ ለማሳደግ መሰራት እንዳለበት ጠቁመው ኤች ዜድ ለቡና አምራች ገበሬዎች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግና ዘንድሮም ለተሻለ ውጤት እና ለውጥ እንትጋ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኤች ዜድ ቡና ላኪ ኃ/የተ/ግ/ ማህበርን
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ እና አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ በጋራ የመሰረቱት ሲሆን ቡናን በከፍተኛ ጥራት በማምረትና በማዘጋጀት ለገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የዉጪ ምንዛሬን በማስገኘት የሚታወቅ ነው።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY