ኩዊንስ ሱፐርማርኬት 11ኛ ቅርንጫፉን በየካ አባዶ አካባቢ አስመረቀ።

የሚድሮክ እንቨስትመንት ግሩፕ አባል የሆነው ኩዊንስ ሱፐርማርኬት በዛሬው ዕለት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የካአባዶ አካባቢ 11ኛ ቅርንጫፉን አስመርቋል።

በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ፣ የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ታረቀኝ ገመቹ፣ የሚድሮክ የየዘርፎቹ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ሚድሮክ እንቨስትመንት ግሩፕ አንደ አዲስ በ2012 ዓ.ም ከተዋቀረ በኋላ ስር-ነቀል ለዉጥ ማስመዝገብ ከቻሉት ድርጅቶች ኩዊንስ ሱፐርማርኬት አንዱ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ጀማል አህመድ ተናግረዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሁሌም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች ላይ ከፊት በመቅደም ሚናውን እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው።

የኩዊንስ ሱፐርማርኬት ዋና አላማ ማትረፍ ሳይሆን ገበያን ማረጋጋት መሆኑን ሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች በመረዳት የተሻለ መስራት እንዳለባቸዉም አቶ ጀማል አሳስበዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ታረቀኝ ገመቹ በበኩላቸው የኑሮ ውድነት አሳሳቢ በሆነበት በዚህ ወቅት በክፍለ ከተማቸው ሁለተኛው የኩዊንስ ቅርንጫፍ በመከፈቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኩዊንስ የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለከተማው ህብረተሰብ የሚያቀርብ ተቋም በመሆኑ ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ ገልፀው ሚድሮክን አመስግነዋል።

አካባቢውም ብዛት ያላቸው መኖሪያ ቤቶችን የያዘ እና የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚገኙበት በመሆኑ ለማህበረሰቡ ጤንነታቸው የተረጋገጡ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ ወተት እና የወተት ተዋጽዖ፣ ስጋ እና የስጋ ውጤቶች እንዲሁም የታሸጉ ምግቦች እና ሌሎች ምርቶችንም በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል፡፡

በዛሬው ዕለት የተመረቀው 11ኛው የኩዊንስ ቅርንጫፍ ለበርካታ ዜጎች ተጨማሪ የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል።
ኩዊንስ ሱፐርማርኬት በደንበኛ የመጎብኘት ቁጥሩን ከመቶ ሺዎች ተነስቶ ዛሬ ላይ በአመት የ3.5 ሚሊየን ደንበኛ ምርጫ መሆን ችሏል፡፡ እስካሁን በአዲስ አበባ በ9 ክፍለ ክተሞች 11 ቅርንጫፎች አሉት፡፡

“እንደ ቤተሰብ” በሚል ቃሉ የከተማችን አዲስ አበባን ነዋሪ የእለት ፍጆታ በበቂ አቅርቦትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማገልገል የኑሮ ውድነትን እና የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይም ይገኛል፡፡

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY