ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቤተሰብ ቀንን በዛሬው እለት ያከበረ ሲሆን መርሃግብሩ ላይ በዙም የቀጥታ የቪዲዮ መልዕክት ያስተላለፉት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀመንበር ሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ምኞቴ ኢትዮጵን ከአደጉ ሀገራት ተርታ ተሰልፋ ማየት ነው ብለዋል።
ይህንን እውን ለማድረግ ሚድሮክ አሁን እየሰራቸው ካሉት የልማት ሥራዎች በተጨማሪ ባለ 10 ኮከብ ሆቴል በመገንባትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሥራዎች በመሥራት ተቋሙ ለሀገር ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ የበለጠ ለማጉላት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የግሉና የመንግሥት ዘርፍ ተናበው በመሥራት የዋጋ ንረትን መከላከል እንዳለባቸው የጠቆሙት ሼይኸ መሀመድ፤ ለሕዝቧ ምቹ የሆነች፣ ለጠላቶቿ የማትንበረከክና በአለት ላይ የጸናች ሀገር ለመገንባት በአንድነት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለፉት ስድስት ዓመታት ያስመዘገበው ውጤት በጣም የሚያኮራ መሆኑን በመግለጽ ለተቋሙ ሠራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።
በተለይም ሚድሮክ አሁን ላይ ከ80 ሺህ በላይ ሠራተኞች ያሉት መሆኑን ጠቁመው፣ ይህንን ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በተጨማሪም ሁሉም የሚድሮክ አመራርና ሠራተኛ የልማት ሠራዊት በመሆን ተቋሙ ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲያስመዘግብ በባለቤትነት ስሜት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ- የሀገር ሀብት
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀ መንበር ሼይኸ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ኢትዮጵያ ከአደጉት የዓለም ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ሚድሮክ የበኩሉን አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ ይገኛል አሉ።
Recent News
-
MIDROC Week Exhibition Kicks Off at Meskel Square!
-
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ በሊሙ በሚገኙ የእርሻ ማሳዎች ያሰራቸውን መኖሪያ ቤቶች ለሰራተኞች አስረከበ።
-
ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በድጋሚ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ በመመረጥዎ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ቤተሰብ ልባዊ ደስታዉን ይገልጻል!
-
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኘው ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰጣቸውን የተለያዩ የበረራ አገልግሎቶች በኦሮሚያ ቱሪዝም ኤግዚቢሽን ሳምንት በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።
Archives
-
Horizon Plantations Launches Eight billion Birr Worth Major Agricultural Investment Project in Somali region.
-
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሠራተኞቹ 1.2 ቢሊዮን ብር ቦነስ መሰጠቱን ገለፁ።
-
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው አህፋ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ድጋፍ አበረከተ።
-
MIDROC Investment group signs agreement with CEMETC GmbH international company
-
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2017/2018 በጀት ዓመት ከአጠቃላይ ሽያጭ የዕቅዱን 99% ማሳካቱን አስታወቀ፡፡
-
Wanza Furnishings Industry obtains ‘Integrated Management System’ certificates.







