የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ሀላ/የተ/የግል ማህበር በአፍሪካ ደረጃ የካይዘን ሥርአትን ተግብረው ለውጥ ከማምጣት አንፃር የተሻለ ውጤት ካስመዘገቡ ድርጅቶች ጋር በመወዳደር በአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

የድርጅቱ መሸለም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ግሩፕ የሚያኮራ ሲሆን ይህንን ውጤት ወደ ሌሎች ድርጅቶች ለማጋባት ጥሩ መነሻ እንደሚሆን ይታመናል።

በሌላ በኩል ድርጅቱ ከአምስት ዓመታት በፊት በከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ የነበረ ሲሆን ባለፉት አራት ዓመታት ግን አትራፊና በተከታታይም በወርቅ ደረጃ ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆን እውቅና ያገኘ ድርጅት መሆን ችሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በግሩፑ ስር እንደሚተዳደር አንድ ድርጅት የተለያዩ የአሠራር ሥርዓቶችን ከመተግበር አንፃር:- የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት፣ የሥራ ላይ ጤናና ደህንነት ሥርዓት፣ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ አመራር ሥርዓት እና የኢንተግሬትድ ማኔጅመንት ሥርዓትን መተግበርም ችሏል።

እንደ ግሩፕ እንዲህ አይነት በአህጉር አቀፍና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ የልህቀት ውድድሮች ላይ ቀዳሚ በመሆን ለሌሎች አርአያ ለመሆን በትጋት የሚሠራ ይሆናል።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY