የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነዉ ዘመናዊ የሕንፃ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ.ማሕበር (MBI) ለገላን ቂልጡ ቆሬ 1ኛደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ፡፡

ዘመናዊ የሕንፃ ኢንዱስትሪ (MBI) በያዝነው ዓመት በገላን ከተማ ዉስጥ ለሁለት የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ለአንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
በዕቅዱ መሰረትም በዛሬዉ እለት ለቂልጡ ቆሬ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቀለም የስቀባለቸዉን መማሪያ ከፍሎችና ለተለያዩ አግልግሎቶች የሚውሉ ብሎኮችን ለትምህርት ቤቱ ሃላፊዎች አስረክቧል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የዘመናዊ የሕንፃ ኢንዱስትሪ (MBI) ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ በዚህ ዓመት ድርጅቱ የማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ለሁለት የ1ኛ ደረጃ እና ለአንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መማሪያ ከፍሎችን ቀለም በመቀባት፣ ችግኞችን በመትከል፣ ለተማሪዎች የዩኒፎርም እና የደብተር ድጋፍ በማድረግ፣ በገንዘብ ተማሪዎቸን በማገዝ እንዲሁም በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ማበረታቻ እንዲሆን ሽልማት በመስጠት ከትምህርት ቤቶቹ እና ከተማሪዎቹ ጎን በመቆም እየሰሩ መሆናቸዉን ገልፀዋል፡፡
በዚህ ድጋፍም ድርጅታችን ዘመናዊ የህንፃ ኢንዱስትሪ ደስተኛ መሆኑንና በድርጅት ብቻም ሳይወሰን የማኔጂመንት አባላቱም በየወሩ ከደመዛቸው ላይ ተቆራጭ በማድረግ የዚህ መልካም ተግባር ተካፋዮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ተማሪዎቹ የነገ ራዕያቸውን ዛሬ ላይ እንዲያልሙ ፕሮግራም በማውጣት በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ተገኝተው ስለ ድርጅቱ አሰራር ጉብኝት እንዲያደርጉ ማድረጉንና ተማሪዎቹ ነገ ፋብሪካውን የሚረከቡት እነርሱ እንደሆኑ አውቀው ዛሬ ላይ ትምህርታቸውን በትጋት እንዲማሩ እነዳበረታቷቸው ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የቀሩትን ሁለቱን የገላን ደምቢ እና መሪኖ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ስራዎችም እየተጠናቀቁ መሆናቸዉን ጠቁመው ድጋፉም ቀጣይነት ያለዉ መሆኑን አረገግጠዋል፡፡
የገላን ቂልጡ ቆሬ 1ኛደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ዘዉዱ ቱራ በበኩላቸዉ ለትምህርት ቤቱ በተደረገው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም የድርጅቱ ድጋፍ እንደማይለያቸው ያላቸውን እምነት በመግለፅ በገላን ከተማ የሚገኙ ሌሎች ድሪጅቶችም መሰል በጎ ድጋፎችን በማድረግ ትዉልድን የመቅረፅ ስራ ዉስጥ ኢንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የትምህርት ቤቱን ተማሪዎች በመከወል ንግግር ያደረጉት ተማሪ ብርሃን አበበ እና ተማሪ ሳምራዊት ደበላ ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ በመደረጉ ደስ መሰኘታቸውን ገልፀው ድጋፉ ቀጣይነት ባለዉ መልኩ መደረግ ኢንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይም የችግኝ ተከላ ተከናውኗል፡፡

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE